From Wikipedia, the free encyclopedia
ሊንጎናውያን (ሮማይስጥ፦ ሊንጎኔስ) በጥንታዊ ጋሊያ (የአሁን ፈረንሳይ አገር ያኽል) የተገኘ የኬልቶች ብሔር ነበረ። ዋና ከተማቸው አንደማንቱኑም ሲሆን ይህ ከተማ በኋላ «ሊንጎኔስ» በመባል እና ዛሬ ላንግረ ተብሎ ይታወቃል።
በ410 ዓክልበ. ግድም ከሊንጎናውያን አንዳዶቹ በስሜን ጣልያን በፖ ወንዝ አካባቢ ወዳለው አገር ፈለሱ። በ398 ዓክልበ. ሮሜ ከተማን ከበዘበዙት ነገዶች መካከል እንደ ተሳተፉ ይመስላል።
በጋሊያ የቀሩት ሊንጎናውያን በ፩ናው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የሮማውያን ባሕል ተለመዱ። የራሳቸውን መሐልቆች ሠሩ። በ61 ዓ.ም. የሮሜ ታሪክ ጸሐፊ ታኪቱስ እንደ ገለጸው፣ እነዚህ ሊንጎናውያን በተከሠተው የባታውያ ዓመጽ ተሳተፉ።
ጸሐፊው ሴክስቱስ ዩሊዩስ ፍሮንቲኑስ እንዳለው፣ በሮሜ ንጉሥ ዶሚቲያኑስ ዘመን (73-88 ዓ.ም.) ሊንጎኔስ እጅግ ሀብታም ከተማ ሆኖ በዩሊዩስ ኪዊሊስ መሪነት አመጸ። የንጉሡ ሠራዊት ሲቀርብ ኗሪዎቹ ሊንጎናውያን ከተማቸው እንዳይፈርስ ፈርተው ነበር። አንዳችም ነገር ስላልተጎዳ ግን ተደንግጠው ወደ ታማኝነት ተመለሱና ፸ ሺህ ወታደሮች አስረከቡ።
በ፩ኛውና ፪ኛው ክፍለ ዘመናት ከሊንጎናውያን ብሐር ፪ ኮሆርት (ሠራዊቶች) ለሮሜ መንግሥት ነበሯቸው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.