ቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት
From Wikipedia, the free encyclopedia
ለአለም ጽሕፈቶች ወላጅ ሆነው የሚታስቡ 2 ተመሳሳይ ጽሕፈቶች ተገኝተዋል፣ እነሱም «ጥንታዊ የሲና ጽሕፈት»ና «የዋዲ ኤል ሖል ጽሕፈት» ይባላሉ። «ዋዲ ኤል ሖል» በ1999 እ.ኤ.አ. በግብፅ ተገኝቶ ዕድሜው ከክ.በ. 1800 ዓመት የሚገመት ሲሆን፣ የጥንታዊ ሲና ጽሕፈት በ1904 እ.ኤ.ኣ. በደብረ ሲና በኩል ተገኝቶ ከክ.በ. 1500 ዓመት የተጻፈ ይታመናል።