ታላቁ አልፍሬድ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ታላቁ አልፍሬድ (ጥንታዊ እንግሊዝኛ፦ Ælfrēd፤ 840-892 ዓ.ም. ገደማ የኖሩ) ከ863 ዓ.ም. እስከ 892 ዓ.ም. ድረስ የዌሴክስ ንጉሥ ነበሩ። እርሳቸው መጀመርያ 'የንግሊዞች ንጉሥ' ተባሉ። 'ታላቁ' የተባሉት አገራቸውን ከዴንማርክ ከመጡት ወራሪዎችና ቫይኪንጎች ስለ ተከላከሉ ነው።
ከዚህ በላይ የእንግሊዝ ንጉሥ አልፍሬድ ክርስቲያንና ዕጅግ የተማሩ ሊቅ ሲሆኑ አያሌው መጻሕፍት ከሮማይስጥ ወደ እንግሊዝኛ አስተረጎሙ፣ እንዲሁም የአገራቸውን ሕገ መንግሥት አሻሻሉ። ይህም ሕገ መንግሥት ወይም ዶም ቦክ በመጀመርያ ክፍሎቹ ከአስርቱ ቃላትና ከሕገ ሙሴ (ከኦሪት ዘጸአት 21 & 22) ተመሠረተ። ዋና ከተማቸው ዊንቼስትር፣ እንግሊዝ ነበረ።