ትሪጎኖሜትሪ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ትሪጎኖሜትሪ የሚለው ቃል ከግሪክ የመጣ ( ትሪጎኖን = ሦሥት ጎን፣ ሜትሪ = መለካት) የሶስት ጎኖችን ማዕዘናትና አቃፊ ጎኖቻቸውን ተዛምዶ የሚያጠና የሒሳብ ክፍል ነው። እኒህ ተዛምዶዎች ብዙ ጊዜ የሚገለጡት በትሪጎኖሜትሪክ ፈንክሽን ሲሆን ጥናቱ በአጠቃላይ ለተደጋጋሚ ክስተቶች ጥናት፣ በተለይ ለሞገዶች ከፍተኛ ጥቅም አለው። ስለሆነም የትሪጎኖሜትሪ ጥናት ሰፊ ለውጥ ያሳየው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3ኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ጂዎሜትሪን ለሥነ ከዋክብት ጥናት መጠቀም በጀመሩበት ጊዜ ነበር.[1] ። I
በአሁኑ ወቅት፣ ትሪጎኖሜትሪ ለሒሳብ፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሥነ ከዋክብት ጥናትና ለመሬት ጥናት የሚያግለግል ዋና የሒሳብ መሳሪያ ነው።