ግብረ ስጋ ግንኙነት
From Wikipedia, the free encyclopedia
ግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም ሩካቤ ስጋ ማለት በሴትና በወንድ መካከል ለስሜት እርካታ የሚደረግ ግንኙነት ወይም ፍቅር መሥራት ነው። ይህም ለመባዛት ወይም ለመዋለድ አስፈላጊ ከመሆኑ በላይ የወሲብን እርካታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሊሆን ይችላል።
በሥነ ሕይወት ዘርፍ ሲታይ ወሲብ፣ የእንስትን (ሴትን) እና የተባእትን (ወንድን) ዘር በማዋሃድ ወይንም በማዳቀል፣ የፍጡራን ዝርያ (species)፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሮ የቸረችው ተፈጥሯዊ ተግባር ነው። በእያንዳንዱ የፍጡር ዝርያ ተባእትና እንስት ፆታዎች ይገኛሉ። እነዚህ ፆታዎች በየራሳቸው ዘርን ማስተላልፍ የሚችሉብት ልዮ የማዳቀያ ህዋሳትን በአካላቸው ወስጥ ይሠራሉ ወይንም ያዘጋጃሉ።
እነዚህ ልዮ ህዋሳት 'ጋሜት' (gametes) በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ልዩ ህዋሳት በአካልቸው ተመሳሳይ (በተለይ isogametes በመባል የሚታወቁት) ሊሆኑ ቢችሉም፣ ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ ከተባእትና እንስት የሚገኙት የዘር ህዋሳት በቅርፃቸውም ሆነ በአኳኋናቸው ይለያያሉ። የወንዱ የዘር ህዋስ፣ ም'ጥን ያለና በትንሽ ይዘት ብዙ ዘራዊ ምልክቶችን ማጨቅ እንዲችል ሆኖ የተሠራ ሲሆን፣ ይህንንም ይዞ ረጅም ርቀት መጓዝ እንዲችል የፈሳሽ ውስጥ ተስለክላኪነት ባህርይ ወይንም ችሎታ አለው። የሴቷ ልዩ ህዋስ፣ ከወንዱ ህዋስ ጋር ሲስተያይ በአካሉ አንጋፋ ሲሆን፣ ይህ የሆነበትም ምክንያት ተንቀሳቃሽ ሳይሆን የረጋ ከመሆኑም ሌላ፣ ከተባእት ዘር ጋር ከተገናኘ በኋላ በውስጡ ለሚፈጠረው ሽል አስፈላጊውን የማፋፊያ ንጥረ ነገር መያዝ ስላለበት ነው።
የአንድ ፍጡር ፆታ የሚታወቀው በሚፈጥረው የዘር ህዋሥ አይነት ነው። ተባእት ፍጡራን የተባእትን የዘር ህዋሥ (spermatozoa, or sperm) ሲፈጥሩ፣ እንሥት ፍጡራን የእንሥትን የዘር ህዋሥ (ova, or egg cells) ይፈጥራሉ። የተወሰኑ ዝርያዎች፣ የተባእትንም የእንስትንም የዘር ህዋሥ ከአንድ ግላዊ አካል የሚያፈልቁ ሆነው ይገኛሉ። እነዚህ ፍናፍንት (hermaphroditic) በመባል ይታወቃሉ።
አብዛኛውን ጊዜ የአንድ ዝርያ ተቃራኒ ፆታዎች፣ የተለያየ የአካል ቅርፅና የባህርይ ገጽታ ይታይባቸዋል። ይህ ልዩነት ሁለቱ ፆታዎች ያለባቸውን የእርባታ ኃላፊነትና የሚያስከትለውን አካላዊ ተፅእኖ ያንፀባርቃል።