መፈንቅል
From Wikipedia, the free encyclopedia
መፈንቅል የማይልመጠመጥ ጠንካራ እቃ ሲሆን ከደጋፊ ችካል ላይ በመቀመጥ ሸክምን ለማንሳት በሚደረገው ስራ ጉልበትን ለማባዛት ወይም ሸክሙ የሚሄደውን ርቀት ከፍል ለማድረግ የሚጠቅም ቀላል ማሽን ነው። የጥንቱ የግሪክ ሂሳብ ተመራማሪ የነበረው አርክሜድስ፣ የመፈንቅልን ጉልበት የማብዛት ጠባይ በማዳነቅ እንዲህ ብሎ ነበር የምቆምበት ቦታ ስጡኝ እንጂ፣ መሬትን በመፈንቅል አነሳታለሁ። በጥንቱ ግብጽ አናጺወች ወደ 100 ቶን የሚጠጉ የድንጋይ ቅርጾችን በመፈንቅል ያነሱ እንደነበር ታሪክ ይዘግባል [1]።