From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰርጌይ ሚካይሎቪች ብሪን (እንግሊዘኛ: Sergey Mikhailovich Brin፤ ሩስኛ: Сергей (/ሰርገይ/) Михайлович Брин) (ኦገስት 21, 1973 እ.ኤ.አ. ተወለደ) ሩሲያዊ-አሜሪካዊ ሲሆን ጉግልን በመፍጠሩ ይታወቃል።
በሩሲያ የተወለደ ሲሆን፥ ብሪን ከላሪ ፔጅ ጋር ጉግልን ከመጀመሩ በፊት ኮምፒዩተር ሳይንስና ሒሳብ አጥንቷል። ብሪን ባሁኑ ጊዜ የጉግል ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት በመሆኑ ወደ 14.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አለው። ይህም ከዓለም 26ኛ እና ከአሜሪካ 12ኛው ሀብታም ሰው ያደርገዋል።
ሰርጌይ በሞስኮ፣ ሩሲያ ለየይሁዳ ቤተሰብ ተወለደ። 6 ዓመቱ ሲሆን ሰርጌይና ቤተሰቡ ወደ አሜሪካ መጡ። አባቱ ሚካኤል በሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ማቲማቲሻን ሆኖ እስክ ዛሬ ድረስ ያስተምራል። የስርጂ እናት ዩጂኒያ ብሪን ማቲማቲሻንና ሲቭል ኢንጅነር ሆና ለናሳ ትሰራለች። ሳሙኤል የሚባል ታናሽ ወንድምም አለው።
ሰርጌይ በኮምፒዩተር ዕድገት ጊዜ በማደጉ የኮምፒዩተር ፍላጎቱ ከልጅነቱ ነው የጀመረው። መጀመሪያው ያገኘው ኮምፒዩተር አንድ ኮሞዶር 64 ሲሆን ይህንንም ከአባቱ ዘጠነኛው ልደት በዓሉ ላይ ነው ያገኘው። በሒሳብና ኮምፒዩተር ያለውን ተስዕጦም ገና ትንሸ እያለ ነው ያሳየው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በፔንት ብራንች ሞንቴሶሪ ትምህርት ቤት የወሰደ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በኤላኖር ሩዝቬልት ትምህርት ቤት አጠናቋል። ቤተስቡም የሒሳብ ዕውቀቱንና ሩሲያኛው በማዳበር ረድተውቷል። በሴፕቴምብር 1990 እ.ኤ.አ.፣ ሰርጌይ ሒሳብና ኮምፒዩተር ሳይንስ ለማጥናት ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ፣ ኮሌጅ ፓርክ ገባ። በሜይ 1993 እ.ኤ.አ. የባችለር ሳይንስ ካማግኘቱ በኅላ በስኮላርሺፕ ኮምፒዩተር ሳይንስን ለማጥናት ወደ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሄደ። ከዛም ከታሰበው ጊዜ በፊት በኦገስት 1995 እ.ኤ.አ. የማስተርስ ዲግሪውን ተቀበለ። ባሁኑ ጊዜ ግን የፒ.ኤች.ዲ. ጥናቱን ላልተወስነ ጊዜ አቋርጦ ጉግል ውስጥ እየሰራ ይገኛል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.