ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ
የክርስትና ሃይማኖት ታላቅ አባት / From Wikipedia, the free encyclopedia
ባስሊዮስ ዘቄሣርያ በሌላ አጠራሩ ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ (በግሪክ: Ἅγιος Βασίλειος ὁ Μέγας, Ágios Basíleios o Mégas) (በእንግሊዘኛ Basil of Ceasarea ሲነበብ ባዚል ኦፍ ሢዛሪያ)በቀጰዶቂያ የቄሣርያ ኤጲስ ቆጶስ ነበር ። የንቂያን የሊቃውንት ጉባዔ የሚደግፍና አርያኒዝምንና የአፖሊናረስን ተከታዮችን የክርስትና አመለካከት ተቃውሞ ትክክለኛውን መንገድ ያስተማረ ታላቅ አሳማኝ የሃይማኖት ፈላስፋና መሪ ነበር ።
Quick Facts ቅዱስ ባስሊዮስ, የቄሣርያው ኤጲስ ቆጶስ ...
ቅዱስ ባስሊዮስ | |
---|---|
የቄሣርያው ኤጲስ ቆጶስ | |
ስም | ባስሊዮስ ዘቄሣርያ |
የአባት ስም | ቀዳማዊ ባስልዮስ |
የእናት ስም | ኤሚልያ |
የተወለደው | ፫፻፳፩ ወይም ፫፻፳፪ዓ.ም. |
ያረፈበት ቀን | ጥር ፮ ቀን ፫፻፸፩ ዓ.ም. በቀጰዶቂያ ሥንክሳር |
የሚከበረው |
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኦርየንታል ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በኮፕት ቤተክርስቲያን በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በአንግሊካን ኮሚዩነን ሉተራኒዝም |
የንግሥ በዓል |
ጥር ፮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጄኑዋሪ ፩ና ፴ በቤዛንቲን ክርስቲያን ጄኑዋሪ ፲፬ በሰርቢያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ጄንዋሪ ፪ በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታውት ፮ በኮፕት ቤተክርስቲያን |
Close
ቅዱስ ባስሊዮስ ከሃይማኖት ፈላስፋነቱ ሌላ ድሆችንና ኑሮን ማሸነፍ ያቃታቸውን በመንከባከብ ይታወቃል ። በተጨማሪም የማኅበራዊ ኑሮ ፣ የሥርዐተ ጸሎትና የጉልበት ሥራ ለገዳማዊ ኑሮ መመሪያን መሥርቷል ። ባስሊዮስ ከቅዱስ ጳኩሚስ ጋር የማኅበራዊ ገዳማዊነት አባት ተብሎ በምሥራቃዊ ክርስትና ይታሰባል ። ዳሮግን በምሥራቅም በምዕራብም በቅዱስ ደረጃ ነው የሚከበረው ። እነዚህ ሁለት ጎራዎች ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት የሚለውን ስያሜ ከዮሐንስ አፍወርቅና ከግሬጎሪዮ ናዚያንዘስ ጋር ሰተውታል ።