በሌ
From Wikipedia, the free encyclopedia
በሌ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በወላይታ ዞን የሚገኝ ከተማ ነው። ከተማውም በወላይታ ዞን የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የአስተዳደር ዋና ከተማ ሆኖ ያገለግላል። በሌ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ በአዲስ ቡታጅራ-ሶዶ መንገድ ስከሄድ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ይደርሳል። ከወላይታ ዞን ዋና ከተማ ከሶዶ በ38 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ከተማው በአማካይ ከባህር ጠለል በላይ 1500 ሜትር ከፍታ አላው። በሌ በካርታ ስታይ በ6°55'05" ሰሜን እና በ37°31'55" ምስራቅ መካከል ይገኛል።
Quick Facts
በሌ Bale Ambbaa | |
ከተማ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል |
ዞን | ወላይታ |
ወረዳ | ኪንዶ ኮይሻ |
ከፍታ | 1,500 ሜ. |
Close