ቦሌ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚያገለግል አለም አቀፍ አየር ማረፊያ / From Wikipedia, the free encyclopedia
ቦሌ ዓለም አቀፍ የጥያራ ጣቢያ (አውሮፕላን ማረፊያ) በአዲስ አበባ ከተማ በደቡብ-ምሥራቅ አቅጣጫ ከአራዳ በስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የአገሪቱ ዋና አድማሳዊ የንግድና የግንኙነት በር ነው።
ፕሮፌሶር (ዲባቶ) መስፍን አረጋ፣ ቦሌ በኦሮምኛ ቋንቋ ትርጉሙ የሚፈረፈር ወይም የሚሰነጣጠቅ መሬት እንደሆነ ይነግሩናል። እውነትም የአካባቢው ገጸ-ምድር ለአየር ማረፊያ አመቺ ሜዳማ ቢሆንም መሬቱ ግን ረግረጋማ እና መረሬ ነው።