አባል:Russavia/Polandball
From Wikipedia, the free encyclopedia
Polandball (ፖላንድቦል፣ ፖላንድ ኳስ) ወይም countryball (ካንትሪቦል፣ አገር ኳስ) በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ ሚም /meme/ ወይም ባህሪይ ነው። ሚሙ በጀርመን ቋንቋው Krautchan.net ድረ ገጽ በ/int/ የስዕል ሰሌዳ ላይ በሁለተኛው የ2009 እ.ኤ.አ. ዓመት ክፍል ነው የተጀመረው። ሚሙ በብዙ የኢንተርኔት ኮሚኮች /online comics/ ላይ የሚታይ ሲሆን በእነዚህ ኮሚኮች ውስጥ የዓለም አገራት ኳስ በሚመስሉ ድቡልቡል ገፀ-ባህሪዎች ተወክለው እርስ በርሳቸው በተሰባበረ እንግሊዝኛ (በአብዛኛው ጊዜ) ያወራሉ፤ በአገራት ግንኙነቶች ላይ ይቀልዳሉም።