አክሊሉ ሀብተ-ወልድ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰው ሲሆኑ በ ጣልያን ወረራ ጊዜ አምስቱን ዓመት ሙሉ በፓሪስ የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈጻሚ፤ በዠኔቭ በዓለም መንግሥታት ማኅበር የኢትዮጵያ ዋና ጸሐፊ ከድል በኋላም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት እና እስከ አብዮት ፍንዳታ ድረስም በዓፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር ነበሩ። ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ አቃቂ ታስረው ከቆዩ በኋላ ያለፍርድ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ/ም ከስልሳ ሰዎች ጋር በደርግ ተረሽነው ሞቱ።