ኢንተርስላቪክ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኢንተርስላቪክ (Interslavic) ወይም መድዡስሎቭያንስኪ (medžuslovjansky) የስላቪክ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። የተፈጠረው በ፲፱፻፺፰ (1998) ዓ.ም. በኦንድረይ ረችኒክ፣ ጋብሪዬል ስቮቦዳ፣ ያን ቫን ስቴንበርገንና ኢጎር ፖልያኮቭ ነበር። በመጀመርያው ስሙ «ስሎቭያንስኪ» (Slovianski) ነበር። የቋንቋው ስም ከስላቭኛ ቃላት «መድዡ» (መካከል) እና «ስሎቭያንስኪ» (ስላቭኛ) ደርሷል። ዛሬ ከ፭፻ እስከ ፳፻ ሰዎች ይችሉታል።
ቋንቋው በጣም ቀላል ነው። ቃላቱ ከስላቪክ ቋንቋዎች ብቻ የተመሠረተ ነው። የሚጻፈው በላቲንና ቂርሎስ ፊደል ነው።