ኤሌክትሪክ መስክ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የኤሌክትሪክ መስክ በኤሌክትሪክ ቻርጅ ዙሪያ ወይንም ከጊዜ አንጻር በሚለዋወጥ የመግነጢስ መስክ ዙሪያ የሚገኝ የጉልበት መስክ ነው። q1, q2, q3, ... የተሰኙ ቻርጆችን ያቀፈ የቻርጅ ስርዓት ቢሰጥና እና እያንዳንዳቸው ቻርጆች እርስ በርሳቸው የሚያሳርፉትን ጫና ሳይሆን ከውጭ በሚመጣ እንግዳ ቻርጅላይ የሚያሳርፉትን ጫና ለማስላት የሚጠቅም አይነተኛ መንገድ ነው። ይህንም የሚያረገው በእያንዳንዱ የከባቢው ኅዋ ነጥብ ላይ ከየሙላቱ የሚመነጩ ጉልበቶችን በቬክተር ስርዓት በንብብር በመደመርና የቬክተር መስክ በመፍጠርና፣ ያ ቬክተር መስክ በመጭው ቻርጅ ላይ የሚያሳርፈውን ጉልበት በማስላት ነው።
መለኪያውም ኒውተን በኩሎምብ (N C−1) ነው። አልፎ አልፎም በ ቮልት ለሜትር (V m−1) ሲለካ ይታያል። በእያንዳንዷ ነጥብ ላይ ያለው የ መስኩ ጥንካሬ የሚፈተሸው 1ኩሎምብ ፖዚቲቭ የሆነ መፈተሻ ቻርጅ በዚያ ነጥብ ላይ ቢቀመጥ መስኩ የሚያደርስበትን የጉልበት ጫና በማስላት ነው። የመስኩ አቅጣጫ በዚያ ቻርጅ ላይ የሚያርፈው ጉልበት አቅጣጫ ነው። የኤሌክትሪክ መስክ ለኤሌክትሪክ ቻርጅ፣ ልክ ግስበታዊ ፍጥንጥነት ለግዝፈት እንደሆነ ነው።
አንድ የኤሌክትሪክ መስክ ከጊዜ አንጻር የሚቀያየር ከሆነ፣ ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ቻርጅእኑሶች በመስኩ ውስጥ ሲጓዙ፣ በአካባቢው የሚገኘውን የመግነጢስ መስክ ያውካል። በሌላ አነጋገር የኤሌክትሪክና የመግነጢስ መስኮች ግንኙነት የሌላቸው ነገሮች አይደሉም። አንድ ሰው የኤሌክትሪክ መስክ ነው የሚለውን ሌላ ሰው የኤሌክትሪካና መግነጢስ መስክ ነው ብሎ ሊደመደም ይችላል።