ዋሙራ
የኢትዮጵያ ከተማ ነው / From Wikipedia, the free encyclopedia
ዋሙራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በዎላይታ ዞን የምትገኝ ከተማ ናት። ከተማው በካዎ ኮይሻ ወረዳ ምዕራባዊ በኩል ይገኛል። ዋሙራ በካዎ ኮይሻ ወረዳ ከሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች አንዱ ነው። ከተማዋ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እና የመንግስት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እንደ መብራት፣ ንጹህ የህዝብ ውሃ፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የፖስታ አገልግሎት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የጤና ጥበቃ ተቋማት እና ሌሎችም አሏት። ዋሙራ በወላይታ ሶዶ በምዕራብ በኩል በሶዶ - በከሎ ሰኞ - ላሾ መንገድ ወደ ሃላሌ በሚወስደው መንገድ ላይ ይገኛል።[1]