From Wikipedia, the free encyclopedia
የሁሉም መሰረት እቴጌ እሌኒ ናት ........................ 1. እቴጌ እሌኒ አገሯ ጎጃም፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፣ ደብረ ገነት ቀበሌ፣ ምጣድ ቤት ከተባለው ቦታ ነው። እቴጌ እሊኒ የሸዋውን የአፄ ዘርዐ ያቆብ ልጅ አፄ በእደ ማርያምን አግብታ አፄ ናኦድ ተወለደ።
2. አፄ ናኦድ ከእናቱ አገር ጎጃም፣ ለምጨን ነው ሚስት የተለመነላቸው። የጎጃም (ለምጨን) ባላባቷ እቴጌ ናኦድ ሞገሳ እና አፄ ናኦድ ተጋቡ። ጋብቻው አፄ ልብነድንግልን አፈራ።
3. አፄ ልብነድንግል ልክ እንደ አባታቸው እና አያታቸው የጎጃም እመቤት ነው ያገቡት። አፄ ልብነድንግል የጎጃም፣ የእነማይ ተወላጇን እቴጌ ሰብለወንጌልን አግብተው ስምንት ልጆችን ወለዱ።
................................
ሦስቱ የጎጃም እቴጌዎች
ሦስቱ የጎጃም እቴጌዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሥማቸው በጉልህ ሲነሳ ይኖራል። ሦስቱም ጎጃም ውስጥ ቤተክርስቲያን አሰርተዋል።
1. እቴጌ እሌኒ መርጡለማርያም ዮዲት ጊዲት ካፈረሰችው ቤተክርስቲያን ወደ ምዕራብ በኩል ( እዚያው አምባ ላይ) አንድ ቤተክርስቲያን አሰማርታለች፣ አሁንም አለ።
2. እቴጌ ናኦድ ሞገሳ - ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ውስጥ ጌቴ ሰማኔ ( ሰማኒያ ተብሎም ይጠራል) ገዳም ላይ አሻራዋን አስቀምጣለች።
3. እቴጌ ሰብለወንጌል - እነማይ፣ መንገስቶ ኪዳነምህረት ላይ አሻራዋ ይታያል።
መውጫ:- የአፄ ሱስንዮስ ታሪክ ይቀጥላል። አፄ ሱስንዮስ አንዳንዶች እንደሚሉት ኦሮሞ አላነገሰውም፣ ከኦሮሞ አግብቶ አልወለደም ( ከኦሮሞ መውለድ እና ማግባትን በምንም መመዘኛ እየነቀፍሁ አይደለም፣ አማራው ከኦሮሞ ብዙው ተጋብቷል፣ ወልዷል)፣ ቤተመንግሥቱም ይባብ ( አዴት) ነበር።....
እቴጌ እሌኒ የጎጃም ባላባት ስለመኾና ፍራንሲኮ አልቫሬዝ ከዛሬ 500 ዓመታት በፊት ጽፈዋል፡፡ የአልቫሬዝ የኢትዮጵያ ቆይታ ከ1513- 1519 ዓ/ም ነበር፡፡ ቆይታውን "The prester John of the Indies" በሚል ርእስ ጽፎታል። በ1958 ዓ/ም ግርማ በሻህ የተባሉ ጸሐፊ መጽሐፉን ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰውታል፡፡ እኔ ሁለቱም ቅጅ አለኝ፡፡
የመጣጥፍ ፡ ማውጫዎች
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.