From Wikipedia, the free encyclopedia
የቤት ዝንብ ወይም በሳይሳዊ ስሙ "Musca domestica" ሲነበብ ሙስካ ዶሞስቲካ በንዑስ-ክፍለመደብ "Cyclorrhapha" ዉስጥ የሚገኝ በራሪ ነፍሳት ነው። ምናልባትም ከመካከለኛው ምስራቅ በዝግመተ ለውጥ ወደ መላው አለም እንደተስፋፋ ይገመታል። በጣም የተለመደ የበራሪ ነፍሳት አይነት ነው። ጎልማሳ ዝንብ ጠቆር ያለ ግራጫ ሆኖ አራት ቀጥተኛ ጥቁር መስመር በደረቱ ያለው ፀጉራም ሰውነት ኖሮት አንድ ጥንድ ክንፍ አለው። ቀይ አይኖች አሏቸው። ሴቶቹ ግን ትንሽ ተልቀው አይኖቻቸውም መሃከል የበለጠ ክፍተት አለ።
?ዝንብ | ||||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
አልተተመነም (NE) | ||||||||||||||||
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||||
| ||||||||||||||||
''Musca domestica'' Linnaeus, 1758 | ||||||||||||||||
| ||||||||||||||||
ጎልማሳ ዝንቦች ከ 8 - 12 ሚ.ሜ (0.3–0.5 ኢንች) ድረስ ያድጋሉ። ደረታቸው ግራጫ ወይም አንዳንዴ ጥቁር ሆኖ አራት ጥቁር ቀጥተኛ መስመር ከጀርባው አለው። ሙሉ ሰውነታቸው ፀጉር በመሰለ ነገር የተሽፈነ ነው። ሴት ዝንብ ከወንድ ዝንብ ትንሽ ትተልቃለች እንዲሁም በአይኖቿ መካከል የበለጠ ክፍተት አላት። [1]
እጩ እንደሁኔታው ከ 8 - 20 ሚ.ግ ይመዝናል። [2]
ዝንቦች አንድ ጥንድ ክንፍ ብቻ አላቸው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.