የአፍሪቃ አገሮች
ኤርትራ / From Wikipedia, the free encyclopedia
የአፍሪቃ አኅጉር ከዚህ የሚከተለው የአፍሪቃ 53 ነጻ አገሮችና 8 ጥገኛ ክልሎችን ያጠቃለለ ዝርዝር ሲሆን፤ ዋና ከተሞችን፣ ቋንቋቸውን፣ ገንዘባቸውን፣የሕዝቦቻቸውን ብዛት፣ የገጸ ምድራቸውን ስፋትና የብልጽግናቸውን መለኪያ (GDP per capita ) ያካትታል። የአፍሪቃ አህጉር ከምድር ጠቅላላ ስፋት ስድስት በመቶውን፤ ከመሬቷ ደግሞ ወደ ሃያ ተኩል በመቶውን ይሸፍናል። በገጸ ምድር ስፋትና በሕዝብ ቁጥር እስያን ተከትሎ ሁለተኛ መደብን የያዘ አህጉር ነው። እ.ኤ.አ በ 2005 የአፍሪቃ ሕዝቦች ብዛት ከ ዘጠኝ መቶ ሚሊዮን በላይ ወይም ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ አሥራ አራት በመቶ እንደሆነ ተገምቷል። አህጉሩ በሰሜን በሜዲተራንያ ባሕር ፤ በ ሰሜን ምስራቅ የሱዌዝ ቦይ እና የ[[ቀይ ባሕር} ፤ በደቡብ ምስራቅ የሕንድ ውቅያኖስ ፤ በምዕራብ ደግሞ በአትላንቲክ ውቅያኖስ የተከበበ ነው። ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ሕዝብን የሚያጠቃቅሉት የምዕራብ ሰሃራ ግዛት እንዲሁም ከሞሮኮ በስተቀር ሁሉም ነጻ ሉዐላዊ አገሮች የአፍሪቃ ኅብረት አባላት ናቸው።