የዞብል መቃብር
From Wikipedia, the free encyclopedia
የዞብል መቃብር የፈረሱ ዞብል መቃብር ነው። ከፋሲል መዋኛ አጠገብ በስተምስራቅ ይገኛል። ዞብል በአንዳንዶች ዘንድ ተወዳጁ የአጼ ፋሲለደስ ፈረስ መሆኑ ሲታመን አልፎ አልፎ ሌሎች ሰዎች ፈረሱ የፋሲለደስ ልጅ የቀዳማዊ ዮሐንስ ፈረስ ነው ይላሉ። ሆነም ቀረም የዞብል መቃብር በክብ ቅርጽ በቅምብብ የተሰራ መታሰቢያ ሲሆን ከቆይታ ብዛት ጉዳት እየደረሰበትና ዛፎች በመካከሉ እየበቀሉበት እየፈረሰ ያለ ምናልባት ብቸኛው የኢትዮጵያ ፈረስ መዘክር ነው።