የ፳፻፫ ዓ.ም. የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት
From Wikipedia, the free encyclopedia
የ፳፻፫ ዓ.ም. የሊቢያ ሕዝባዊ አብዮት በሊቢያ ውስጥ የተከሰተ እና በሰሜን አፍሪቃ በተከታታይ ከተደረጉ የተለያዩ ሀገራት ፀረ መንግስታዊ አብዮቶች አንዱ ነው። ይህ አብዮት የተጀመረው በእ.አ.አ. 15 ፌብሩዋሪ 2011 ሲሆን በዚሁ ወር መጨረሻ አካባቢ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተባብሶ ታይቷል። አብዮቱ በዋናነት የኮለኔል ሞአመር ጋዳፊን የ42 ዓመታት የስልጣን ላይ ቆይታ በመቃወም ነው። ፀረ መንግስታዊ አገዛዙን በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰቱ አብዮቶች ጋር እንዲያያዝ የሚያደርገው ዋናው ነገር በቱኒዚያ እና ግብፅ የተደረጉ ሕዝባዊ አብዮቶች ተከትሎ መደረጉ ነው። [1]