ያዕቆብ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ያዕቆብ (ዕብራይስጥ፦ יַעֲקֹב, /የዕቆብ/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የይስሐቅና የርብቃ ልጅ ነበረ። የዔሳው መንታ ወንድም ነበር። በሌላ ስማቸው ኤዶምያስ (ዔሳው)ና እስራኤል (ያዕቆብ) የተባሉትን ሁለት ብሔሮች ወለዱ። ያዕቆብ (እስራኤል) ግን የተቀደሠ የመሢህ ዘር ተስፋ ወራሽ ሆነ። ያዕቆብና ሚስቶቹ ከነቁባቶቹ የእስራኤል ፲፪ ነገዶች ወለዱ።
በዕዝራ ሱቱኤል ምዕ. ፬ በአዋልድ መጻሕፍት ዕዝራ የዚህን አለም መጨረሻ ከእግዜር መንግሥት መጀመርያ ምን ይለየዋል ሲጠይቅ፣ መልዐኩ ያዕቆብ ከኤሳው ቀጥሎ እንደ ወጣ (ቅርጭምጭሚት ተጨብጦ) ይከተላል የሚል መልስ ሰጠ።
የያዕቆብ ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ያዕቆብ ሕይወት ብዙ ይጻፋል።