ጌዴኦ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጌዴኦ በኢትዮጵያ ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኝ ብሔር ነው። የጌዴኦ ብሔረሰብ በዋናነት በጌዴኦ ዞን ውስጥ ባሉ ስድስት ወረዳዎች በስፋት የሚኖር ሲሆን ከዞኑ ውጪም በሲዳማ ዞን፣ በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና በጉጂ ዞኖች በሚገኙ አጎራባች አካባቢዎች ወይንም ወረዳዎች በብዛት እንደሚገኙ ይገመታል። የጌዴኦ ብሔረሰብ በዋናነት በሚገኝባቸው የከተማና የገጠር አካባቢዎች ሌሎች የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የሲዳማ፣ የወላይታ በተለይም ደግሞ በከተሞች የጉራጌ እና የስልጤ ብሔረሰብ አባላት ከብሔረሰቡ ጋር በስብጥር ይኖራሉ። በሰሜን ከሲዳማ በደቡብ በምስራቅ እና በምዕራብ ከኦሮሞ ብሔረሰብ ጋር ይወሰናል። በ፲፱፻፺፱ ዓ/ም በተደረገው የቤቶችና ሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 986,977 ነው።
Quick Facts አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት, በስፋት የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ...
አጠቃላይ የሕዝብ ብዛት | |||
---|---|---|---|
986,977 | |||
በስፋት የሚኖሩባቸው አካባቢዎች | |||
| |||
ቋንቋዎች | |||
ሀይማኖት | |||
በአብዛኛው ፕሮቴስታንት ክርስትና፣ ባህላዊ እምነት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና | |||
ተዛማጅ ብሔሮች | |||
Close