ሉግዱስ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ሉግዱስ
Remove ads

ሉግዱስፈረንሣይ አፈ ታሪክ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ንጉሥ ነበረ። የናርቦን ልጅና ተከታይ ይባላል።

Thumb
የኬልቶች ጣኦት «ሉጉስ» በኋላ ዘመን በሦስት መልኮች ይቀረጽ ነበር።

እርሱ የልዮን ከተማ መሥራች እንደ ነበር የሚል ትውፊት አለ። የሮሜ መንግሥት ሰዎች ይህን ከተማ ሉግዱኑም ሲሉት መካከለኛው ፈረንሳይ ከዚህ ከተማ ሉግዱነንሲስ ክልል አሉት። በአንዳንድ መጽሐፍ ደሞ ሉግዱስ የለይድን (በሆላንድ) መሥራች ይባላል።

የሉግዱስ ሌላ ስም ሉዶዊኩስ ሲሆን ይህ እስካሁን ድረስ የዘመናዊ ስም «ሉዊስ» ወዘተ. መነሻ እንደ ነበር ይባላል።

Thumb
በፈረንሳይ የተገኘ የ«ሉጉስ» መሥዊያ

በኋላ የኬልቶች ጣኦት ወይም አምላክ ስም ሉጉስ ሆነ፤ ይህም በኋላ የሮማውያን ሜርኩሪዩስ እንደ ነበር ተቆጠረ። በዚህም ዘመን በአይርላንድ አፈ ታሪክ በአይርላንድ የነገሠው ሉግ ደግሞ የ«ሉጉስ» ሞክሼ ይቆጠራል። በአይርላንድ ትውፊት ግን የአይርላንድ ንጉሥ ሉግ ከቱዋጣ ዴ ዳናን እና ከፎሞራውያን ወገኖች ነው።

ምንጮች ስንት ዓመት እንደ ገዛ በማወራት ይለያያሉ፤ ለ፭፣ ፳፮፣ ፵፮ ወይም ፶ ዓመታት መሆኑ የሚሉ መጻሕፍት ይገኛል። የንጉሥ ሉግዱስ ልጅ ቤሊጊዩስ ተከተለው።

ቀዳሚው
ናርቦን
ኬልቲካ / ጋሊያ ንጉሥ
1879-1854 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ)
ተከታይ
ቤሊጊዩስ
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads