መለስ ዜናዊ

From Wikipedia, the free encyclopedia

መለስ ዜናዊ
Remove ads

መለሰ ዜናዊ (የትውልድ ስማቸው ለገሠ ዜናዊ አስረስ) (ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰው ነበሩ። በአድዋ ትግራይ የተወለዱ ሲሆን ከ፲፱፻፹፯ ዓ/ም አንስተው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በከፍተኛው የአመራር ቦታ ላይ ነበሩ። የኢህአዴግና የሕውሓት ሊቀመንበር በመሆን ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ቆይተዋል።

መለስ ዜናዊ

Quick facts ፕሬዝዳንት, ቀዳሚ ...

አቶ መለስ ዜናዊ አባታቸው (አቶ ዜናዊ አስረስ ከጎዣም አገው ቤተሰባዊ ትስስር እንዳላቸው ይታመናል[1]) የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፣ በእናታቸው በኩል ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው።

መለስ በታወቀው ጀነራል ዊንጌት 2ኛ ደረጃ ተምህርት ቤት የተማሩና ከአጼ አህለስላሴ የኮከብ ተማሪዎች ሽልማት የተሸለሙ፣ ከዛም ወደ በረሃ ወርደው በታጋይነት ከመሰለፍቸው በፊት፤ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሜዲካል ፋክልቲ ተማሪ ነበሩ።  ትግርኛ፣አማርኛና፡ እንግሊዝኛ አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ።

መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ባደረጓቸው አስተዋፅኦዎች የኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው ይባላሉ፡፡ ኢትዮጵያም እንደ እርሳቸው ያለ መሪ አግኝታ እንደማታውቅ በሰፊው ይነገራል፡፡

Remove ads

ወደ ስልጣን አመጣጥ

አቶ መለስ የሚመሩት ሕውሓት የኮሎኔል መንግስቱ ኅይለ ማርያምን አምባገነናዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ሲታገሉ ከነበሩ ድርጅቶች አንዱ ነበር። አቶ መለስ የሕወሓት አመራር ኮሚቴ መሪ ሆነው በ1971 ተመረጡ፤ ቀጥሎም በ1975 የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኑ። የደርግ መንግሥት ከወደቀም ጀምሮ የሕወሓትና የኢህአዴግ ሊቀ-መንበርም ሆነው አገልግለዋል። ኢህአዴግ የአራቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞከራሲያዊ ድርጅት፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ውህደት ነው። ወደ ስልጣን ሲመጡ በጊዜው ላቋቋሙት ጊዜያዊ መንግስት ፕረዚዳንት ሆነው ካገለገሉ በሗላ 1985 ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ። በጊዜው የፕረዚደንትነቱን ቦታ የተረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናችው።

Remove ads

የሽግግር መንግስታቸው

የአምባገነኑ የመንግስቱ ኃይለ ማርያም አስተዳደር እንደ ወደቀ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ኢአሓዴግ በሕዝብ ምርጫ ሳይሆን ብሔረሰቦችን መሰረት ባደረገ በጥቂት ግለሰቦች የሽግግር መንግሥቱ በመቋቋሙና በተለይም የአማራን ሕዝብ(የአማራን የፖለቲካ አስተሳሰብ) ያለው ፖርቲ ሳይወከል መቅረቱ አብዛኛውን ሕዝብና ምሁራንን በጣም አስቆጣ።

የኢህአዴግ ደጋፊዎች

በወቅቱ በአምባ ገነኑ ደርግ ስር ተጨቁኖ ለነበረው ድሃ ኢትዮጵያዊ የኢህአደግ ወደ ስልጣን መምጣት ሌላ አማራጭ ስላልነበር የኢሕአዴግን መንግስት ሕዝቡ ለመቀበል ስለ ተገደደ በጊዜው ኢህአዴግ ይህ ነው የተባለ ተቃውሞ አልገጠመውም። በአንጻሩ ከጅምሩ በትጥቅ ትግል ኢሕአዴግን ሲረዱ የነበሩ የአረብና የምዕራባውያን መንግስታት ከጎንህ አለን በማለት በሁለት እግሩ አንዲቆም አስችለውታል።

ይሁን እንጂ እያደር ሲመጣ የአቶ መለሰ ዚናዊ መንግስት የታገለለትን ዓላማ ስቶ ዲሞክራሲን በማፈን የነጻ ፕሬስ አፈና በማካሄድና የብአዊ መብት ረገጣ ስላበዛ ብዙ የምዕራባዊያን ድጋፍና ከማጣቱም በላይ የብዙ ሺ ኢትዮጵያዊያን ለስደት ዳርጎአል። ሆኖም ዓለም አቀፉን ሽብርተኛ ለመታገል በሚል ሽንገላ ሱማሌን በመውረሩ ምክንያት በጆርጅ ቡሽ የምትመራ አሜሪካ ቀንደኛና ዋነኛ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆና ቀርታለች። ቀጣዩ የአሜሪካ መሪ ባራክ ኦባማም የአገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ካላቸው ፍላጎት አልቃይዳንና አልሸባብ የተባሉ የአክራሪ እስላም ቡድኖችን እየታገልኩ ነው ላለው ኢሕአዴግን ድጋፋቸውን ቀጥለዋል።

የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads