መላሽ አስረካቢ

From Wikipedia, the free encyclopedia

መላሽ አስረካቢ
Remove ads

አስረካቢ ƒ ከ X ወደ Y እሚያስረክብ ቢሆን፣ የ ƒ መላሽ አስረካቢ ƒ1, በተቃራኒ አቅጣጫ Y ን ወደ X, የሚያስረክብ ነው። ሁሉም አስረካቢዎች መላሽ አስረካቢ የላቸውም። መላሽ አስረካቢ ካላቸው ግን ተመላላሽ ይሰኛሉ።

Thumb
አስረካቢ ƒ እና መላሹ ƒ–1. አስረካቢ ƒ ግቤት a ን ለ 3 ስለሚያስረክብ, መላሹ ƒ–1 3 ን ለ a ያስረክባል.

አንድ አስረካቢ ተመላላሽ የሚሆነው አንድ ለአንድ አስረካቢ ከሆነና ከሆነ ብቻ ነው።

ለምሳሌ አስረካቢ ƒ በዲግሪ ሴልሲየስ C የተቀመጠን ሙቀት መጠን ወደ ፋረን ሃይት F ቢቀይር, የዚህ አስረካቢ መላሽ ƒ−1. የሙቀት መጠንን ከፋረርሃይት F ወደ ሴልሲየስ C መልሶ ያመጣል ማለት ነው።

ከአንድ ለአንድ ውጭ ያሉ የአስረካቢ አይነቶች (እንደ ትርፍ አስረካቢዎች፣ እና እንስ አስረካቢዎች)፣ ግዛቶቻቸውንና ጥምር ግዛቶቻቸውን በማስተካከል ተመላላሽ አስረካቢዎች ሊሆኑ የሚችሉበት መንገድ ሊዘጋጅ ይቻላል።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads