መነን አስፋው
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
እቴጌ መነን አስፋው የቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባለቤት ነበሩ። ግርማዊ እቴጌ መነን መጋቢት 25 ቀን 1883 ዓም በወሎ ጠ/ግዛት በአምባሰል አውራጃ ልዩ ስሙ ዕጓ ከተባለው ቀበሌ ከጃንጥራር አስፋውና ከወ/ሮ ስሂን ሚከኤል ተወለዱ። እቴጌ መነን በልጅነት ዘመናቸው በእናት በእባታው ቤት መምሀር ተቀጥሮላቸው ኣማርኛ ማንበብና መፃፍ ጠንቅቀው አወቁ። በተጓዳኝ ልዩ ልዩ የቤት ባልትና ሙያዎችን ተምረው በማጠናቀቃቸው የቤት ራስ ለመባል በቅተዋል።
==
==
መነን የሚለው ቃል በዐማርኛ የሴት ልጅ ስም ሲሆን ታላቁ ምሁር ዓለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ ቀጭን ፈታይ፣ ባለሟያ፤ ወይም መልከ መልካም፤ ትክክል ፍጽምት ሕጸጽ የሌለባት ማለት እንደሆነ አፍታትተው አሥፍረውታል።[1]
Remove ads
ማጣቀሻዎች
ዋቢ ምንጮች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads