ቨርጂኒያ

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ቨርጂኒያ (እንግሊዝኛ፦ Virginia፤ አሜሪካዊ አጠራር፦ /ቭርጅኘ/) ከአሜሪካ 50 ክፍላተ ግዛቶች አንዷ ስትሆን ዋና ከተማዋም ሪችመንድ ይባላል። የዚህ ክፍላተ ግዛት ታላቅ ከተማ ቨርጂኒያ ቢች ወይም የቨርጂኒያ ባህር ጠረፍ ይባላል። ቨርጂኒያ ሙሉ ስሙ የቨርጂኒያ ኮመንዌልዝ ይባላል።

Quick facts
Remove ads

ታሪክ

አሜሪካ አብዮት በኋላ፣ ቨርጂኒያ በ1780 ዓ.ም. ክፍላተ ግዛት (ስቴት) ሆነች። ከዚያ በፊት የታላቋ ብሪታኒያ ቅኝ ግዛት (ኮሎኒ) የነበረች ሲሆን በዚህ መልኩ የተመሰረተችውም በ1599 ዓ.ም. ነበር።

አሜሪካ እርስ በርስ ጦርነት ከመካሄዱ በፊት ዌስት ቨርጂኒያ የዚህች ክፍላተ ግዛት አካል ነበር። ሆኖም ከጦርነቱ በኋላ ዌስት ቨርጂኒያ በመገንጠል ቨርጂኒያ እራስዋ የአሜሪካ ኮንፌዴሬት ግዛቶች አባል ሆነች፤ ሪችመንድም የኮንፌዴሬት ዋና ከተማ ሆነች። ይችም ሪችመንድ ከዋሺንግተን ዲሲ በጣም ሩቅ አይደለችም። ምዕራባዊው ክፍል በአንጻሩ የዩኒየን ኃይሎች ታማኝ በመሆን፣ በጦርነቱ መካከል በ1856 ዓ.ም. የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ለመሆን በቃ። ዩኒየን ኃይሎችን ለመደገፍ የተገነጠሉት የምዕራቡ ክፍሎች ከእንደገና ቨርጂኒያን ለመዋሃድ አልፈቀዱም፣ ስለሆነም እስካሁን ድረስ እራሳቸውን ችለው ይገኛሉ። ከጦርነቱ በኋላ በ1862 ዓ.ም. ምሥራቁም ዳግመኛ ቨርጂኒያ ተብላ ልትገባ ተፈቀደች።

8 የአሜሪካ ፕሬዜዳንቶች ቨርጂንያ የተወለዱ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር ከማንኛውም የአሜሪካ ክፍላተ ግዛቶች ይበልጣል።

Remove ads

ማጣቀሻ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads