ተመስገን ገብሬ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ተመስገን ገብሬ የተወለዱት በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረ ማርቆስ ከተማ በ፲፱፻፪ ዓ/ም ነው፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተ ክህነት ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ቤተሰባቸው ካህናት ከመሆናቸውም በላይ ጎበዝ ተማሪ ነበሩ። ጉብዝናቸው በዘመናዊ ትምህርት ሲከታተሉም ጎልቶ ወጥቷል፡፡ ከጎጃም አዲስ አበባም በመምጣት በስዊድን]] ሚሲይናዊ ትምህርት ቤት ተማሩ በወቅቱ ሀገሪቱ ካፈራቻቸው ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ፡፡ ተመስገን በጋዜጠኝነት ሙያ ከመሥራታቸውም በላይ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኃላፊነት ቦታ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት በአርበኝነት ከጠላት ጋር ተፋልመዋል፡፡ በኋላም ወደ ሱዳን ተሰደው ገዳሪፍ ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያዊያንን በልዩ ልዩ መልክ አስተምረዋል፡፡ ጣሊያን ከለቀቀች በኋላ የዘመናዊ አስተሳሰብና ዕድገት ዓላማዋ ዕውን እንዲሆንም ፍፁም የለውጥ አርበኛ ሆነው ሠርተዋል።
ተመስገን፣ ኅዳር ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ/ም በ አዲስ አበባ ነፃነት ማተሚያ ቤት “የጉለሌው ሰካራም” በሚል ርዕስ ያሳተሙት ድርሰታቸው የመጀመሪያው፣ የታተመ የአማርኛ አጭር ልብ-ወለድ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ የጉለሌው ሰካራም ከመታተሙ በፊት ስለ የካቲቱ ፋሺስታዊ ጭፍጨፋ (ግፊቱን በቀመሱት አርበኛው ደራሲ አገላለጽ፣ ‹‹ዓለም በድንገት ተለውጣ፣ አዲስ አበባም ኢጣሊያኖች ኢትዮጵያውያንን የሚያርዱበት ቄራ ሆና ነበር፡፡››) “የካቲት ፲፪” በሚል ርዕስ እና “ሊቀ-ጠበብት እውነቱ” የተሰኙ ሁለት አጫጭር ልብወለዶችን በጋዜጣ ላይ አውጥተዋል፡፡[1] ከዚህም ሌላ ‹‹ሕይወቴ›› የተሰኘውን ግለታሪካቸውን ያዘጋጁት አርበኛው አቶ ተመስገን ገብሬ በአምስቱ ዓመት የፋሺስት ወረራ ጊዜም በደረሱት ‹‹በለው በለው አትለውም ወይ፤ የጥቁር አንበሳ አይደለህም ወይ›› በሚለው መዝሙራቸውም ይታወሳሉ፡፡ [2]
Remove ads
ማጣቀሻ እና ዋቢ ምንጮች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads