ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)

From Wikipedia, the free encyclopedia

ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)
Remove ads

ኃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) 1928 ዓ.ም ከአባቱ መርጌታ ገ/ዮሐንስ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አካባቢ ተወልዶ በልጅነቱ የቤተክርስቲያን ትምህርት ቀስሟል። መደበኛ ትምህርቱን በምኒሊክ ት/ቤት እየተከታተለ በስላሴ ቤተክርስቲያን በድቁና ያገለግል የነበረው ገሞራው፤ በልጅነቱ የተካነበት የግእዝ ቋንቋ ከቀሳውስቱ ጋር እንደፈለገ በቅኔ እንዲግባባ አስችሎታል። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘውን መንፈሳዊ ኮሌጅ ተቀላቀለ። ከመንፈሳዊ ትምህርት ይልቅ ፍልስፍና ቀልቡን ስለገዛው ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ተቋም ተቀይሮ የሚወደውን ስነ ጽሁፍ ማጥናት ቀጠለ።

የደራሲና ባለቅኔው ስራዎች በጥቂቱ “አንድነት ግጥም” (እማማ አፍሪካን ለማስታወስ)፣ “በረከተ መርገም”፣ “የበሰለው ያራል”፣ “በናቴኮ ሴት ነኝ”፣ “እናትክን በሉልኝ”፣ “የሽግግር ደባ”፣ “ዛር ነው በሽታዋ”፣ “ቅኔ ለዘመን”፣ “ቆርጠሃት ታለለ”፣ “የመንጎል ጥሪ”፣ “ዜሮ ፊታውራሪ” ይሰኛሉ።[1]

Thumb

አንድነት ግጥም (እማማ አፍሪካን ለማስታወስ) 1984 87 ገጽ
በረከተ መርገም 1987 ISBN 91-7328-627-3 96 ገጽ
የበሰለው ያራል 1988 ISBN 91-7328-638-9 224 ገጽ
በናቴኮ ሴት ነኝ 1989 243 ገጽ
እናትክን በሉልኝ 1989 ISBN 91-7328-774-1 134 ገጽ
የሽግግር ደባ (?) 1990 ISBN 91-7328-675-3 353 ገጽ
ዛር ነው በሽታዋ 1991 208 ገጽ
ቅኔ ለዘመን 1992 ገጽ274
ቆርጠሃት ታለለ (?) 1992 290 ገጽ
የመንጎል ጥሪ 1994 ISBN 91-630-2924-3 108 ገጽ ]]
ዜሮ ፊታውራሪ 1995 ISBN 91-7328-768-7 55 ገጽ ]]

Remove ads

ሌሎቸ ስራዎች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads