ነፋስ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ነፋስ
Remove ads

ነፋስ ሁለት አይነት ትርጉሞች አሉት። በመሬት ላይ፣ ንፋስ የሚባለው የአየር እንቅስቃሴ ነው። ከመሬት ውጭ ባለው ጠፈር ንፋስ የሚባለው የአየር ወይንም የተለያዩ እኑሶችን እንቅስቃሴ ነው። ለምሳሌ ከፀሐይ ፈንድተውና ተስፈናጥረው ወደ ጥልቁ ኅዋ የሚጓዙት እኑሶች ፀሐያዊ ነፋስን ይፈጥራሉ። በፀሐይ ሥርአተ ፈለክ(ፕላኔት) ውስጥ ከፍተኛ ነፋስ የሚነፍስባቸው ኔፕትዩንሳተርን ናቸው።

Thumb
የነፋስን አቅጣጫና ፍጥነት መለኪያ አኔሞሜትር

ነፋስ እንደ ሃይሉና የሚውስደው ጊዜ እንዲሁም እንደ እርጥበቱ ይከፈላል፡፡ ከክፍሎቹም ውስጥ

  • ለምለም ነፋስ- ቀስ ብሎ የሚነፍስ ነፋስ
  • ልክስክስ ነፋስ - አቧራ ወደላይ አንስቶ ለትንሽ ደቂቃ ካንከባለለ በኋል በቶሎ የሚጠፋ
  • ወዠብ ነፋስ - ዝናብ የሚቀላቅል ነፋስ
  • አውሎ ነፋስ (ዊርል ዊንድ፣ ቶርኔዶ) - በኃይል እየተሽከረከረ የተለያዩ እቃዎችን ወደሰማይ እያጎና አደጋ የሚያደርስ
Remove ads

የነፋስ ተፈጥሮ

Thumb
አንድሩ አውሎ ንፋስ የፈጠረው ጥፋት

በመሬት ላይ የሚፈጠሩ ነፋሶች ምክናያታቸው የአየር ጫና ልዩነት ነው። በሁለት አካባቢዎች መካከል የተለያየ የአየር ጫና ሲኖር፣ ልዩነቱ እስኪጠፋ ድረስ አየር ክከፍተኛ ጫና ወደ ዝቅተኛ ጫና ይሰደዳል። በሚሰደድበት ውቅት ነፋስን ይፈጥራል። ሞቃታማ የአየር ክፍል ከቀዝቃዛ የአየር ክፍል ያነሰ ጫና ስላለበት ብዙ ጊዜ ነፋስ የሚነፍሰው ከቀዝቃዛ ክፍል ወደ ሞቃታማ ክፍል ነው። ስለሆነም ነፋስ ብዙ ጊዜ ቀዝቃዛ ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ በቋሚነት ለሚነፍሱ ነፋሶች ተጠያቂዎቹ ሁለት ምክንያቶች ናቸው። አንደኛው በምድር ወግብ እና በምድር ዋልታዎች መካከል ያለው የሙቀት ልዩነት ሲሆን ሁለተኛው የመሬት በራሷ ዛቢያ ላይ መሽከርክር ነው።

አንስተኛ የአየር ጫና ልዩነት ባለባቸው አካባቢዎች ለምለም ነፋስ ወይን ቀሰስተኛ ነፋስ ይፈጠራል። ሆኖም ከፍተኛ ልዩነት ባለባቸው አካባቢዎች እስከ 200 ማይል በሰዓት የሚጓዝ እጅግ ፈጣን አውሎ ነፋስ ይፈጠራል። በዚህ ፍጥነት የሚጓዝ ነፋስ ቤቶችን እስከማፍረስ እና ህይወት እስከማጥፋት ሃይል ይኖረዋል።

Remove ads

ነፋስ ኃይል

Thumb
ይህ የነፋስ እሽክርክሪት ነፋስን በመጠቀም ኤሌክትሪክ ያመነጫል

በታሪክ አንጻር የስሪ ላንካ ሰዎች፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት 300 ዓ.ዓ. ጀምረው የንፋስን ሃይል ሙቀት ለመፍጠርና ብረትን ለማቅለጥ እንደተጠቀሙበት ይጠቀሳል[1]። እኒህ ምድጃዎች በሞንሱን ነፋስ መንገድ ላይ የሚነቡ የነበር ሲሆን የሚፈጥሩት ሙቀት እስከ 1200 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርስ ነበር። ከሺህ አመት በኋላ የመጀመሪያው በሥራ ላይ የዋለ የነፋስ ወፍጮ አፍጋኒስታን ውስጥ በ7ኛው ክፍለ ዘመን (ከክርስቶስ ልደት በኋላ) እንደተሰራ ይጠቀሳል። [2] የኒህ ወፍጮዎች ጥቅም እህልን ለመፍጨትና ውሃን ከጉድጓድ ለማውጣት ነበር።[3] ከ1170ዎቹ ጀምሮ በሰሜን-ምዕራብ አውሮጳ ክፍሎች የነፋስ ወፍጮወች በሰፊው ጥቅም ላይ መዋል ጀመሩ።

በአሁኑ ወቅት የነፋስ ኤሌክትሪክ ማመንጫውች በአለም ላይ እየተሰራጩ ሲሆን አቅዳቸውም ከድሮዎቹ የነፋስ ወፍጮወች ይመነጫል። ከመሬት እየተራቀ በሄደ ቁጥር የነፋስ ፍጥነት እየጨመረና አስተማማኝም እየሆነ ስለሚመጣ ብዙ ኩባንያዎች ከከባቢው አየር በጣም ከፍ ብሎ ያለውን ነፋስ ለኤሌክትሪክ ምንጨታ ስራ እንዴት እንደሚያውሉት እያጠኑ ይገኛሉ። ጥናቱ ስኬት ካመጣ የአለምን የሃይል ፍላጎት በዚህ መንገድ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት ይቻላል[4]

Remove ads

አውሎ ንፋስ

የአውሎ ንፋስ ዓይነቶች በፉጂታ መለኪያ

መለኪያ የንፋስ ፍጥነት ተደጋግሞ የመከሰቱ መጠን ሊያደርሰው የሚችለው የጥፋት አይነት
ማይልስ በሰዓትmph ኪሎሜትር በሰዓትkm/h
EF0 65–85105–13753.5% አንስተኛ ወይንም ምንም ጥፋት

በአሸንዳ ላይ ትንሽ ጉዳት፣ ከጣሪያ ላይ ትንሽ ነቅሎ መውሰድ፣ የዛፎች ቅርንጫፎች መሰበር፣ ጥልቅ ስር የሌላቸው ዛፎች ተገፍተው ይወድቃሉ

Thumb
EF0 ለምሳሌ የሚያደርሰው ጥፋት
EF1 86–110138–17831.6%መካከለኛ ጥፋት

ጣሪያዎች በሃይል ይገለባሉ፣ ተንቀሳቃሽ ቤቶች ይገለበጣሉ፣ የውጭ በሮች ይገነጠላሉ፣ መስኮት እና ሌሎች መስታወቶች ይሰበራሉ

Thumb
EF1 ለምሳሌ የሚያደርሰው ጥፋት
EF2 111–135179–21810.7%ከበድ ያለ ጥፋት

በደምብ ከተሰሩ ቤቶች ላይ ጣሪያወች ተገንጥለው ይሄዳሉ፣ የፍሬም ቤቶች መሰረት ይናወጣል፣ ተንቀሳቃሽ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ይወድማሉ፣ ትላልቅ ዛፎች ይቀስፋሉ፣ ወይንም ከስራቸው ይመነገላሉ፣ ተስፈንጣሪ አደጋ ጣይ እቃዎች በአየር ውስጥ የፈጠራሉ፣ መኪናዎች ከመሬት ይነሳሉ

Thumb
EF2 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF3 136–165219–2663.4%ከባድ ጥፋት

በጥሩ ሁኔታ የተሰሩ ቤቶች ይፈርሳሉ፣ ትላልቅ ፎቆችና እና ህንጻዎች፣ ሞሎች፣ ከፍተኛ አደጋ ይደርስባቸዋል፣ ባቡሮች ይገለበጣሉ፣ ዛፎች ከቅርፊታቸው ይላቀቃሉ፣ ከባባድ መኪናዎች ከመሬት ተነስተው ይወረወራሉ፣

Thumb
EF3 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF4 166–200267–3220.7%ከፍተኛ ጥፋት

በደምብ የተሰሩና ሙሉ ፍሬም ያላቸው ቤቶች ሙሉ በሙሉ ይወድማሉ፣ መኪኖችና ሌሎች ትላልቅ ነገሮች ይወረወራሉ፣ ትናንሽ ሚሳኤሎች ይፈጠራሉ፡

Thumb
EF4 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF5 >200>322<0.1%ሙሉ በሙሉ ውድመት

ጠንካራ ፍሬም ያላቸውና በጥሩ ሁኔታ የተሰሩ ቤቶች ይወድማሉ፣ መሰረታቸው ተጠርጎ ይጠፋል፣ በፌሮ የጠነከሩ የኮንክሪት ቤቶችና ግንቦች በሃይል ይጎዳሉ፣ ረጃጅም ህንጻዎች ይፈርሳሉ፣ ወይንም ከፍተኛ መዋቅራዊ ጉዳት ይደርስባቸውል።

Thumb
EF5 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
Remove ads

ተጨማሪ ንባቦች

ማጣቀሻ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads