አለቢዮን
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
አለቢዮን (ግሪክኛ፦ Ἀλεβίων) ወይም አልቢዮን (Ἀλβίων) በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ የፖሰይዶን ልጅና የበርጊዮን (ደርኩኖስ) ወንድም ሲሆን እርሱና በርጊዮን በሄራክሌስ ላይ ውግያ በሊጉርያ ተዋጉ። ይህ ሄራክሌስ የጌርዮን ከብት በኢቤሪያ (የእስፓንያ ልሳነምድር) ማርኮ ወደ ግሪክ አገር ሲመለስ ነበር ይባላል።[1]
በውግያው አልቢዮንና በርጊዮን ታላቅ ሠራዊት ነበራቸው፣ የሄራክሌስም ሠራዊት ሲቸገር ሄራክሌስ ለአባቱ (ዜውስ) ጸልዮ አሸነፈ፤ ሁለቱም ወንድማማች ተገደሉ።[2][3]
በእንግላንድ አፈ ታሪካዊ ልማዶች ደግሞ ይህ አልቢዮን የታላቅ ብሪታንያ ግዛት በአባቱ ኔፕቱን ወይም በአያቱ ኦሲሪስ ተሰጥቶ ከሳሞጤስ ተወላጆች ወሰደው። ከዚህ የተነሣ ታላቅዋ ብሪታንያ ደሴት መጀመርያ ስሙን «አልቢዮን» ተቀበለ። ወንድሙም በርጊዮን ያንጊዜ በአየርላንድና በኦርክኒ ደሴቶች ይገዛ ነበር። በመጨረሻ ሄርኩሌስ ሊቢኩስ ሁለቱንም ወንድማማች በሮን ወንዝ በኩል በውግያ ገደላቸው።
Remove ads
ዋቢ ምንጮች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads