እስክንድርያ

From Wikipedia, the free encyclopedia

እስክንድርያ
Remove ads

እስክንድርያ ወይንም አሌክስዳንድርያ331 ዓክልበ.ታላቁ እስክንድርንግድ ማዕከል ለመሆን የተመሰረተች የጥንቱ ዘመን ታላቅ ከተማ ነበረች። በግብጽ አገር በግሪኮች የተመሰረተችው ይች የባህር ጠረፍ ከተማ በዘመኑ በምድር ላይ ከነበሩት ሁሉ ታላቅ የነበረውን የእስክንድርያ ቤተ መጻሕፍት በመያዝ ትታወቃለች። ስለሆነም ብዙ ስማቸው እስካሁን የሚጠሩ የግሪክ ተመራማሪዎች በዚች ከተማ ኖረዋል። ታዋቂው የጂዎሜትሪ ተማሪ ዩክሊድ በዚች ከተማ ይኖር እንደነበር ይጠቀሳል። በሌላ ጎን የጥንቱ ዘመን አለም አቀፍ አሰድናቂ የሚባለው የባህር ፋኖስ በዚሁ ከተማ ይኖር ነበር። እስክንድርያ፣ ከተቆረቆረ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 1000 ዓመታት የግብፅ ዋና ከተማ በመሆን አገልግሏል። በኋላ ግብጽ በመስሊሞች ስትወረር ዋና ከተማው ወደ ፉስታት ካይሮ ተዛወረ።

Thumb
Quick facts
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads