አንጥያኮስ አፊፋኖስ

የሴሉሲድ ግዛት ንጉስ (175-164 ከክርስቶስ ልደት በፊት) From Wikipedia, the free encyclopedia

አንጥያኮስ አፊፋኖስ
Remove ads

፬ኛ አንጥያኮስ አፊፋኖስ (ግሪክኛ፦ /አንቲዮኾስ ሆ ኤፒፋኔስ/) ከ183 እስከ 172 ዓክልበ. ድረስ የሴሌውቅያ መንግሥት ንጉሥ ነበር። «ኤፒፋኔስ» ማለት በትዕቢቱ እንደ ተመካ «የአምላክ ክሥተት» ማለት ነው። እንደ ወፋፌ እና ጨካኝ ንጉሥ ይታወሳል።

Thumb
የአፊፋኖስ መሐለቅ

አፊፋኖስ የአይሁድናን ሃይማኖት ያሳደደ ንጉሥ ነበር። ከአይሁዶቹ አያሌዎች «ግሪካዊ-አይሁዶች» ሲባሉ እነኚህ የአይሁድ ሃይማኖትና ባህል ንቀው የግሪክ ባህልና ቋንቋ ደጋፊዎች ነበሩ። ሌሎች የአይሁድ ወገኖች እንደ መቃብያን በአይሁድና ባህል ቀሩ። አፊፋኖስ አይሁድናን ለማጥፋት ከግሪካዊ-አይሁዶች ጋራ ተባብሮ ነበር። ከመቃብያን ወገን ጋር ብሔራዊ ጦርነት ሆነ፣ ብዙ አይሁዶችም ተገደሉ። ይህም ንጉሥ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ የግሪኮች ጣኦታት አስገባ።

በግሪኩ መጻሕፍተ መቀባውያን አፊፋኖስን ይተርካል፣ በመጨረሻ የሞተው አንጀቱ ከሥፍራው ሲወድቅ ነበር። በኢትዮጵያ ያሉ መጻሕፍተ መቃብያን ደግሞ ጺሩጻይዳን ብለውት እንደ ጠቀሱት ይታመናል። በብዙ መሐለቅ ላይ ከምስሉ አጠገብ የታተመባቸው ከተሞች «ጺር (ቲሮስ) ኡ (እና) ጻይዳን (ሲዶና)» ስለተጻፈ ነበር።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads