ኣጣርድ

የመጀመሪያው ፕላኔት ከፀሐይ From Wikipedia, the free encyclopedia

ኣጣርድ
Remove ads

ኣጣርድ ወይም ሜርኩሪ፡ (ምልክት፦☿) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት ቅርቡ (1ኛው) ነው። ከበስተኋላው ዘጠኙም ፈለኮች ማለትም ቬነስመሬትማርስጁፒተርሳተርን ኡራኑስነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ።ሜርኩሪ ጠንካራ ፣ የብረት ሰልፋይድ የውጪውን ንጣፍ ፣ ጥልቀት ያለው ፈሳሽ ንጣፍ እና ጠንካራ የውስጥ ኮርትን የሚሸፍን ጠንካራ የሰልፈር ክሬን እና ምንጣፍ ያለው ይመስላል።

Thumb

ስሙ «ኣጣርድ» የተወረደ ከአረብኛው «ኡጣሪድ» ነበር። በድሮ ጊዜ ይህ የአረመኔ ጣዖት ስም ነበር። አሕዛብ ይህ የጥበብ ጣኦት እንደ ነበር ስላመኑ፣ የፈለኩ ስም ከዚህ ጣኦት ስም መጥቶ በየቋንቋው ይለያይ ነበር። ስለዚህ የፈለክም ሆነ የጣኦት ስም በፋርስኛ «ቲር»፣ በባቢሎንኛ «ናቡ»፣ በጥንታዊ እንግሊዝኛ «ዎደን»፣ በግሪክ «ሄርሜስ»፣ በሮማይስጥም «ሜርኩሪዩስ» ሆነ። «ሜርኩሪ» የሚለው እንግሊዝኛ ሲሆን ከዚሁ ሮማይስጥ ስም መጣ። በዕብራይስጥ ግን ስሙ «ኮካብ ሐማህ» ወይም «የፀሐይ ኮከብ» ይባላል። በአፋን ኦሮሞ ደግሞ «ቃሙ ዳለቸ ወይም ኡርጂ ጋንፉሬ» ሲባል ፍቺውም « ግራጫ በረሃ ወይም ፈጣን ኮከብ» ነው። በሶማለኛ ደግሞ «ዱሳ» ይባላል።

Remove ads

ይዘት

ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፈለኮች በመጠኑ ትንሹ ነው። ዲያሜትሩ 2439.7 ኪ.ሜ ብቻ ነው። መዋቅሩ ከመሬት ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ቋጥኞች የበዙበት ነው።

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads