አትክልት

From Wikipedia, the free encyclopedia

አትክልት
Remove ads

ዕፅዋት ከሕያዋን ነገሮች አምስቱ ዋና ዘርፎች አንዱ ናቸው። ምግበለፊ ውኑክለስ ናቸው፣ ይህም ማለት የራሳቸውን ምግብ ይሰራሉ እና ውስብስብ ወይም ባለኑክለስ ህዋስ (ሴሎች) ያላቸው ናቸው። አብዛኞቹ ዕፅዋት ከስፍራ ወደ ስፍራ መዛወር እንደ እንስሶች አይችሉም። ሲበቅሉ ግን እጅግ ቀስ ብለው ይዞራሉ።

Thumb
ቢጫ አበባ

በዕፅዋት ዘርፍ ውስጥ ታዋቂ አይነቶች ዛፍዕፅቊጥቋጥሣርሐረግፈርንሽበትአረንጓዴ ዋቅላሚ ይገኛሉ። በዕፅዋት ጥናት ዘንድ፣ አሁን 350,000 ያሕል የዕፅዋት ዝርያዎች ይኖራሉ። ፈንገስ እና አረንጓዴ ያልሆነ ዋቅላሚ ግን እንደ ዕፅዋት አይቆጠሩም።

አብዛኛዎቹ ዕፅዋት በመሬት ውስጥ ይበቅላሉ፣ አገዳቸው ከላይና ሥራቸው በታች አላቸው። አንዳንድ በውኃ ላይ ሰፋፊዎች ናቸው። ውኃና ምግብ የሚያገኙ በሥሮቻቸው በኩል ነው፤ ከዚያ በአገዳ ወጥተው እስከ ቅጠሎች ድረስ ሲጓዙ ነው። በቅጠሎች ውስጥ በሚገኙት ትንንሽ ቀዳዳዎች ውኃ በፀሐይ ዋዕይ በመትነን፣ ውኃው በአገዳው መንገድ ምግብን ከታቹ ወደ ላይ ይስባል። ይህም ስበተ ቅጠላበት ይባላል።

ዕፅዋት ምግብን እንዲሠሩ፣ የሚያስፈልጉዋቸው የፀሐይ ብርሃን፣ ካርቦን ክልቶኦክሳይድ፣ የመሬት ማዕድንና ውኃ ነው። አረንጓዴው ሃመልሚል (ክሎሮፊል) የፀሐይቱን አቅም ይወስዳል።

እንደ እንሥሣት፣ ዕፅዋትም የእንስትና የተባእት የዘር ህዋስ (gamete) ያመነጫሉ። በተጨማሪ፣ ብዙ የዕፅዋት አይነቶች ወሲባዊ በማይሆን ዘዴ መስፋፋትና መባዛት ይችላሉ። ይህ እፃዊ ተዋልዶ ይባላል።

Remove ads

ሥነ ሕይወታዊ ክፍፍሎች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads