ኮሮናቫይረስ
የቫይረስ ዐይነተ-ዐባል From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ኮሮናቫይረሶች በአጥቢዎች እና በአዕዋፍ ላይ በሽታ የሚያስከትሉ የቫይረሶች ስብስብ ናቸው። ኮሮናቫይረሶች በሰዎች ላይ እንደጉንፋን ያሉ ቀለል ያሉ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን እንዲከሰት ሲያደርጉ አንድ አንድ ጊዜ ደግሞ እስከ ሞት የሚያደርሱ እንደ ሳርስ ፣ መርስ ፣ እና ኮቪድ-19 ዓይነት ከባድ በሽታዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። የሚያስከትሉት የበሽታ ምልክቶች በሌሎች እንስሶች ላይ የተለያዩ ናቸው። በዶሮዎች ላይ ለምሣሌ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲያስከትሉ በላሞች እና አሳሞች ላይ ተቅማጥን ያስከትላሉ። እስካሁን ድረስ ሰዎችን የሚያጠቁትን ኮሮናቫይረሶችን የሚከላከሉ ወይም የሚያከሙ ክትባት ወይም የጸረ-ቫይረስ መድኃኒቶች የሉም።
Remove ads
ግኝት
ኮሮናቫይረሶች ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኙት እ.ኤ.አ 1960ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ነው።[1] መጀመሪያ የተገኙት በዶሮዎች ላይ ተላላፊ የብሮንካይቲስ ቫይረሶች እና በሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉንፋን የሚያስከትሉ ቫይረሶች ነበሩ። [2] ከዚያም በመቀጠል እ.ኤ.አ. 2003 እንደ SARS-CoV ፣ በእ.ኤ.አ. 2004 HCoV NL63 ፣ በእ.ኤ.አ. 2005 HKU1 ፣ በእ.ኤ.አ. 2012 MERS-CoV ፣ እናም በእ.ኤ.አ. 2019 SARS-CoV-2 (ወይም በቀድሞ አጠራሩ 2019-nCoV) ዓይነት ያሉ ተመሳሳይ ቫይረሶች ተገኝተዋል። ከነዚህም አብዛኛዎቹ ከባድ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን አስከትለዋል።
ዋቢ ምንጮች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads