ወለተ ጴጥሮስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታዋቂ ከሆኑት አንስት ቅዱሳን አንድዋ ናት ። ገድልዋ በሺ፮፻፷፬ ዓ.ም.የተጻፈ ሲሆን የምትታወቀውም በተለይ የሮማን ካቶሊሲዝም በምድረ ኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን በተደረገው ፍልሚያ ሕዝቡ ሃይማኖቱን እንዳይቀይር በማስተማር ፣ በየደብሩ እየደበቀች ከሞት ጥቃት በማዳን ፣ እንዲሁም የሃይማኖት ማኅበረሰቦችን በመመሥረት ፣ ተአምራቶችን በማድረግ ነው ።
ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አባቷ ባሕር አሰግድ እናቷ ደግሞ ክርስቶስ አዕበያ ይባላሉ። ትውልዷ ከዳሮ /ምስራቅ ኢትዮጵያ/ ወገን ነው። ወንድሞቿ ዮሐንስና ዘድንግል በንጉሥ ሱስንዮስ ጊዜ ታላላቅ ባለስልጣናት ነበሩ። እናት አባቷ በህግ በስርዓት ካሳደጓት በኋላ ሥዕለ ክርስቶስ የሚባል የዓፄ ሱሰኒዮስ የጦር አበጋዝ ቢትወደድ አግብታ ፫ ልጆች መውለድዋን ገድሏ ይናገራል። ይህ ቢትወደድ ይኖርበት የነበረው ግንብ ቤት ፍራሽ እስከ አሁን ድረስ በጋይንት ስማዳ ይታያል።
Remove ads
ከሮማን ካቶሊሲዝም ጋር ትግሉዋ
ወለተ ጴጥሮስ ከቢትወደድ ሥዕለ ክርስቶስ ጋር በሰላም በመኖር ላይ እያለች ንጉሡ ዓፄ ሱሰኒዮስ የተዋሕዶ ሃይማኖቱን ቀይሮ በሮማውያን መምህራን በመሰበክ ካቶሊክነትን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ህዝብም ካቶሊክ እንዲሆን ዐወጀ ። [1] በዚህ ዐዋጅ የተነሣ በንጉሡ ደጋፊዎችና የቀደመ ሃይማኖታችንን አንለቅም ባሉት እውነተኛ የተዋህዶ ምዕመናን መካከል ታላቅ ጠብ ሆነ። የንጉሡ ሠራዊትም በተዋሕዶ ምእመናን ላይ ዘመቱ። ቢትወደድ ሥዕለ ክርስቶስ ከዘመቻ ሲመለስ የጳጳሱን የአቡነ ስምዖንን ልብስ እንደግዳይ ሰለባ ለንጉሡ ይዞለት መጣ። ይህንን የሃይማኖቷን መናቅ የአባቶቿን መደፈር የተመለከተችው ወለተ ጴጥሮስ እንደዚህ ካለው ከሀዲ ጋር በአንድ ቤት አብሮ መኖር አያስፈልግም ብላ ቆረጠች። ከዚህም በኋላ ከቤቱ የምትወጣበትን ዘዴ ያለ እረፍት ማሰላሰል ጀመረች:: ከዚያም ወደ ገዳም ለመግባት እንዲረዷት ከጣና መነኮሳት ጋር መላላክ ጀመረች። የጣና ቂርቆስ ገዳም አበምኔት አባ ፈትለ ሥላሴም ወለተ ጴጥሮስን ይዘዋት እንዲመጡ ሁለት መነኮሳትን ላኩ። በዚያ ጊዜ ልጆቿ ሁሉ ሞተውባት ነበር። ወለተ ጴጥሮስ ከመነኮሳቱ ጋር መጥፋቷን ያወቀው ቢትወደድ ሥዕለ ክርስቶስ ይዘው ያመጡለት ዘንድ አያሌ ሠራዊት ከኋላዋ ሰደደ። ነገር ግን ወለተ ጴጥሮስና ሁለቱ መነኮሳት በእግዚአብሔር ረዳትነት በዱር ውስጥ ተሰውረውባቸዉ ሊያገኟቸው አልቻሉም። ይህ ተሰውረውበት የነበረዉ ቦታ እስከዛሬ ድረስ ሳጋ ወለተ ጴጥሮስ ይባላል። በኋላ ዘመንም በስሟ ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶበታል።
Remove ads
ምንኩስናዋና ተጋድሎዋ
ከዚህ በኋላ ወደ ደብረ ዕንቁ ገዳም ገብታ ስርዓተ ምንኩስናን ተምራ መነኮሰች። ታላቁ ገድሏ የተጀመረውም ከዚህ በኋላ ነው። ወለተ ጴጥሮስ ከምንኩስናዋ በኋላ በመላ ሀገሪቱ እየተዘዋወረች ሕዝቡ በተዋህዶ እምነት እንዲፀና፣ በጸሎተ ቅዳሴም ጊዜ ሃይማኖቱን የለወጠው የንጉሡ የሱስንዮስ ስም እንዳይጠራ ትመክር ጀመር። ብዙ ሰዎችም በምክሯ ተስበው በሃይማኖታቸው እየጸኑ ሰማዕትነትን መቀበል ያዙ።
ይህንን የወለተ ጴጥሮስን ተጋድሎ የሰማው ንጉሥ ሱስንዮስ ተይዛ ለፍርድ ትቀርብ ዘንድ ብዙ ወታደሮች በየአካባቢው አሰማራ። በመጨረሻም በሰራዊቱ ተይዛ በሱስንዮስ ፊት ቀረበች። መሳፍንቱ መኳንንቱና ለእንጀራቸው ሲሉ ሃይማኖታቸውን የለወጡ ሊቃውንት በተሰበሰቡበት ትመረመር ጀመር።
Remove ads
በቁም እሥር ላይ
ከሳሽዋ " ንጉሡን ካድሽ፣ እግዚአብሔርን ካድሽ፣ ትዕዛዙን እምቢ አልሽ፣ ሃይማኖቱን ዘለፍሽ፣ሌሎች ሰዎችም ሃይማኖቱን እንዳይቀበሉ ልባቸውን አሻከርሽ" ሲል ከሰሳት። ወለተ ጴጥሮስ ግን እንደ አምላኳ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በከሳሾቿ ፊት ዝም አለች። ንጉሡም ርቃ እንዳትሄድ ነገር ግን ከቅርብ ዘመዶቿ ጋር እንድትኖር / የቁም እስር/ ፈረደባት።
ሃይማኖት ተንቃ፣ ቤተ ክርስቲያን ተዋርዳ የመናፍቃን መጨዋቻ ስትሆን ማየት የሃይማኖት ፍቅርዋ ያላስቻላት ወለተ ጴጥሮስ በግዞት መልክ ከተቀመጠችበት ቦታ ጠፍታ ዘጌ ገዳም ገባች። አብርዋትም ወለተ ጳውሎስና እህተ ክርስቶስ የተባሉ እናቶች ነበሩ። በዚያም በገዳሙ የነበሩ መነኮሳት እና የአካባቢው ምእመናን በተዋህዶ ሃይማኖታቸው እንዲጸኑ እየመከረች ጥቂት እንደቆየች የሚያሳጧትና የሚከሷት ስለበዙ ቦታውን ለቃ ወደ ዋልድባ ገዳም ገባች። ዋልድባ ገብታ ሱባዔዋን ከፈጸመች በኋላ በገዳሙ የነበሩትን አባቶችና እናቶች በእምነታቸው ጸንተው እንዲቆዩ ትመክራቸው ጀመር።
አጼ ሱስንዮስ የወለተ ጴጥሮስን ተጋድሎ፣ መነኮሳትንና ምእመናንን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ፣ የካዱትም ከክህደታቸው እንዲመለሱ ማድረጓን ሲረዳ ብዙ ወታደሮችን ይልክባት ነበር። በዋልድባ እያለችም የንጉሡ ሰራዊት ሊያስኖሯት ስላልቻሉ ወደ ጸለምት አመራች። በጸለምት የወለተ ጴጥሮስ ትምህርት እንደ ሰደድ እሳት ተስፋፋ። ምእመናን እየውደዷትና እየተቀበሏት እራሳቸውን ለሰማዕትነት አዘጋጁ። ይህንን የሰማው ሱስንዮስ ይቺ ሴት እኔ ብተዋት እርሷ አልተወችኝም፣ አለና የጸለምቱን ገዥ ባላምባራስ ፊላታዎስን ወለተ ጴጥሮስን ይዞ እንዲያመጣለት አዘዘው።
ወለተ ጴጥሮስ በጸለምቱ ገዥ ተይዛ ወደ ሱስንዮስ መጣች። አስቀድመው ሃይማኖቷን እንድትለውጥ ሊያግባቧት ሞከሩ። እርሷ ግን ጸናች። ሦስት የካቶሊክ ቀሳውስት መጥተው ስለሃይማኖትዋ ተከራከሯት። ወለተ ጴጥሮስ ግን የሚገባቸውን መልስ ሰጥታ አሳፈረቻቸው። በየቀኑ የካቶሊክ ቀሳውስት ሃይማኖቷን ትታ ካቶሊክ እንድትሆን በምክርም በትምህርትም ለማታለል ሞከሩ። ይሁን እንጂ ወለተ ጴጥሮስ በተዋሕዶ ዓለት ላይ ተመስርታ ነበርና ፍንክች አላለችም፡፡
ሃይማኖቱዋን ለማስቀየር
በመጨረሻ አንዱ የካቶሊክ ቄስ "እርሷን እቀይራለሁ ማለት በድንጋይ ላይ ውኃ ማፍሰስ ነው" ሲል ለንጉሡ አመለከተ። ሱስንዮስ ይህንን ሲሰማ ሊገላት ቆረጠ። አማካሪዎቹ ግን "አሁን እርስዋን ብትገል ህዝቡ ሁሉ በሞቷ ይተባበራል፣ ስለ ሃይማኖቱ እንደ እርሱዋ መስዋዕት ይሆናል። ደግሞ ሰው ሁሉ ካለቀ በማን ላይ ትነግሣለህ? ይልቅስ ታስራ ትቀመጥ።" ብለው መከሩት። ንጉሡም ገርበል ወደተባለው በርሃ ሊልካት ወሰነ።
መልክዐ ክርስቶስ የተባለው ዋነኛ የካቶሊኮች አቀንቃኝ ወደ ሱስንዮስ ፊት ቀርቦ "ንጉሥ ሆይ በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ ክረምቱ እስኪያልፍ ድረስ ከእኔ ጋር ትክረም። እኔ እመክራታለሁ። የፈረንጆቹ መምህር አልፎኑስም ሁልጊዜ መጽሐፉን ያሰማታል። ይህ ሁሉ ተደርጎ አሻፈረኝ ካለች ያንጊዜ ግዞት ትልካታለህ" ሲል ለመነው ንጉሡም ተስማማ።
መልክዐ ክርስቶስ ወለተ ጴጥሮስን የካቶሊኮች ጳጳስ ወደሚኖርበት ጎንደር አዘዞ ወሰዳት። ሁለቱ ተከታዮቿ ወለተ ክርስቶስ እና እኅተ ክርስቶስ አብረዋት ሰነበቱ። ወለተ ጳውሎስ ዘጌ ቀርታለች። አልፎኑስሜንዴዝም ዘወትር እየሄደ የልዮንን ክህደት ያስተምራት ነበር። ንጉሡም የወለተ ጴጥሮስን ወደ ካቶሊክነት መቀየር በየጊዜው ይጠይቅ ነበር፣ የሚያገኘው መልስ ግን ሁልጊዜ አንድ ነው "በፍጹም"። ክረምቱ አለፈ። ኅዳርም ታጠነ። ወለተ ጴጥሮስም በትምህርትም በማባበልም ከተዋሕዶ ሃይማኖቷ ንቅንቅ አልል አለች። ስለዚህ ወደ ስደት ቦታዋ ገርበል በርሃ በሱስንዮስ ወታደሮች ተጋዘች። ወለተ ጴጥሮስ ብቻዋን ገርበል ወረደች። በእርጅና ላይ ያለችው እናቷ ይህንን ስትሰማ አንዲት አገልጋይ ላከችላት። ቆራጧ ተከታይዋ እኅተ ክርስቶስም ወዲያው ወደ እርሷ መጣች።
Remove ads
በገርበል በረሃ
ገርበል በርሃ ለ፫ አመት ስትኖር ብዙ ጊዜ ትታመም ነበር። ስለዚህ መከራውን ሁሉ ስለሃይማኖቷ ቻለችው። ከግዞቱ ከተፈታች በኋላ ደንቢያ ውስጥ ጫንቃ በተባለ ቦታ ተቀመጠች። በስደቱ ምክንያት ቆባቸውን አውልቀው የነበሩ አያሌ መነኮሳትም ስደቱ መለስ ሲል በዙሪያዋ ተሰበሰቡ: በገዳማቸዉም ፀንተዉ እንዲኖሩ ትመክራቸዉ ነበር።በኋላም ወደ ጣና ቂርቆስ ተጉዛለች።ከዚያም ምጽሊ ወደተባለው ደሴት ሄዳ በዙርያዋ አያሌ መነኮሳትን ሰብስባ ለሃይማኖታቸዉ እንዲጋደሉ መከረቻቸዉ።። ነገር ግን መከራ ያልተለያት ወለተ ጴጥሮስ መዝራዕተ ክርስቶስ የተባለው ሰው ካቶሊክ ያልሆኑ ምእመናንን አስገድዶ የሚያስጠምቅበትን ደብዳቤ ይዞ ወደ አካባቢው መምጣቱን ስለሰማች መነኮሳቱን መክራና አስተምራ ወደ እየበረሃው ከሰደደች በኋላ እርሷም እንደገና ስደት ጀመረች። ተመልሳ ወደ ምጽሊ የመጣችው አገር ሲረጋጋ በ፵፱ አመቷ ነው።
Remove ads
ከስደት መልስ
ከስደት ስትመለስ መኖርያዋ ያደረገችው መንዞ የተባለውን ቦታ ነው። በዚያ ቦታ ላይ በጸሎትና በስግደት ተጠምዳ ኖረች። በምጽሊ ገዳም አብሯት የነበረው የደብረ ማርያም አበምኔት አባ ጸጋ ክርስቶስም መጽሐፈ ሐዊን ይተረጉምላት ነበር።
አጼ ሱስንዮስ ምላሱ ተጎልጉሎ ከእግዚአብሔር ቅጣቱን ሲቀበልና የተዋሕዶ ሃይማኖት ስትመለስ አቡነ ማርቆስ ግብጻዊው ጵጵስና ተሹመው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ከመንገድ ላይ ጠብቃ ቡራኬ ተቀበለች። እርሳቸውም ሊቀ ዲያቆናት አድርገው ሾሟት። ስለሃይማኖቷ ብላ ከባሏ መለየትዋ እና መከራ መቀበሏ እስከ ግብጽ ድረስ መሰማቱን ጳጳሱ ነግረዋታል።
የመጨረሻ ሕይወት ታሪኳ
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads