የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮች

From Wikipedia, the free encyclopedia

የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮች
Remove ads

የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮችሰላማዊ ውቅያኖስ የሚገኝ የደሴቶች አገር ነው። ዋና ከተማው ፓሊኪር ነው።

Quick facts የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮችFederated States of Micronesia ...

ዋናው ኢንዱስትሪ ከውቅያኖስ አሣ በተለይም ጦን ማጥመድ ነው። የመቆያ ግብርና ብቻ አለ፤ ዋና ምርቶቹም ኮኮነት ዘምባባሙዝአሬካ ዘምባባካሳቫስኳር ድንች ናቸው። እንግሊዝኛ የሥራ ቋንቋና መደበኛው ቋንቋ ነው፤ የተለያዩ የልዩ ልዩ ደሴቶች ኗሪ ቋንቋዎች አሉ።

Remove ads

ታሪክ

Thumb
የኗሪዎች ሰላምታ ሥነ ስርአት

ዙሪያው ለ1100 እስከ 1600 ዓም ግድም ድረስ የሳውደዩር መንግሥት ተባለ፤ በዚያም ጊዜ ኢሶከለከል ለተባለ አሸናፊ እንደ ወደቀ በአፈ ታሪክ ይባላል። የኢሶከለከል ሥርወ መንግሥት እስከ 1878 ዓም ድረስ ቆየ፤ ከዚያ በኋላ የእስፓንያ ቅኝ ግዛት ሆነ። አውሮጳዊ ተጓዦች ግን ከ1522 ዓም ጀምሮ በመርከብ ይጎበኙ ነበር። የእስፓንያ ቅኝ ግዛት መሆኑ ከ1878 እስከ 1891 ዓም ቆየ፣ በ1891 ዓም ለጀርመን መንግሥት ተሸጠ። በ1906 ዓም አንደኛው የዓለም ጦርነት ሲጀመር ጃፓን ደሴቶቹን ከጀርመን ያዛቸው፤ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ግን በ1936 ዓም አሜሪካ ከጃፓን ያዛቸው። ከጦርነቱ በኋላ በይፋ የተመድ አደራ ተብሎ በአሜሪካ አስተዳደር ስር እስከ 1979 ዓም ድረስ ቆየ።

Remove ads

ማጣቀሻ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads