ደቡብ አፍሪካ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ደቡብ አፍሪካ
Remove ads
Quick Facts Republic of South Africa የደቡብ አፍሪካ ሬፑብሊክ ...
Remove ads

ቋንቋዎች

በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ።

መንግሥት

ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውንብሉምፎንቴንፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው።

ባሕል

ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው።

የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ።

የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስክሪኬት እና ራግቢ ናቸው።

በአገር ቤት ሜዳዎች አንበሣቀጭኔጉማሬጅብአውራሪስ ሞልተው ሊታዩ ይቻላል።


Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads