ዶመኒካ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ዶመኒካ የካሪቢያን ባህር ደሴት አገር ሲሆን ዋና ከተማው ሮዞ ነው።
የሀገሩ ዋና ምርት ሙዝ ነው፣ እንዲሁም የኮኮነት፣ ብርቱካን ሌሎችም ፍራፍሬ ይመረታሉ። በቅርብም ጊዜ ቡና፣ ሬት፣ ማንጎ፣ ፓፓያ ተጨምረዋል። የሳሙናም እንዱስትሪ አለ። የአገር ሥራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ቢሆንም የሕዝብ መነጋገሪያ የዶመኒካ ፈረንሳይ ክሬዮል ነው። በዶመኒካ ባሕል አበሳሰል አሣ በሊጥ ጥብስ፣ የበቆሎ ገንፎ፣ ሙዝ ጥብስ፣ ስኳር ድንች፣ ድንች፣ አተር በሩዝ፤ ቡናማ ወጥ ዶሮ፣ [[በሬ] በሽንኩርትና ካሮት ወጥ ይወደዳሉ።
በአገሩ ታሪክ፣ እስከ 1682 ዓም ድረስ የደሴቶች ኗሪዎች የካሪቦች ብሔር አውሮጳውያን እንዳይሠፍሩባቸው ከለከሉ። በቋንቋቸው ዶመኒካን «ዋይጡ ኩቡሊ» ይሉት ነበር። የፈረንሳይ ሰዎች በ1682 ዓም ሠፈሩበት፣ ዩናይትድ ኪንግደም በጦርነት በ1753 ዓም ያዘው፣ እንደገና ከ1770 እስከ 1775 ዓም ድረስ ወደ ፈረንሳይ ተመለሰ፤ ከዚያም ጀምሮ የዩናይትድ ኪንግደም ቅኝ ግዛት ሆኖ እስከ 1970 ዓም ድረስ ቆይቶ ነበር። በ1970 ዓም አገሩ የዩናይትድ ኪንግደም ንግሥት ትቶ ነፃ ሪፐብሊክ ሆነ።
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads

