ዶን ወንዝ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
የዶን ወንዝ (ሩስኛ፦ Дон) በሩሲያ የሚገኝ ዋና ወንዝ ነው። መነሻው ኖቮሞስኮቭስክ በሚባለው ከተማ ሲሆን እስከ አዞቭ ባሕር ድረስ የፈስሳል።
በጥንታዊ ዘመን አገሩ እስኩቴስ በተባለው ጊዜ ግሪኮች ወንዙን «ጣናይስ» አሉት። የግሪክ ነጋዴዎች ጣናይስ የተባለ ቅኝ ከተማም በአፉ መሠረቱ።
ከ1722 ዓ.ም. አስቀድሞ ይህ ወንዝ የአውሮፓና የእስያ ጥንታዊ ጠረፍ ሆኖ ይቆጠር ነበር። በዚያን አመት የአውሮፓ ጠረፍ እስከ ኡራል ወንዝ እንዲዘረጋ የሚል ሀሣብ ለመጀመርያ ጊዜ ቀረበ።[1]
በመጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት (9፡2፣ 6፣ 13) ከምሥራቁ ጫፍ («ራፋ») ጀምሮ በአዞቭ («ሜአት» ወይም «ሜኦት») ባሕር ወዳለው እስከ አፉ ድረስ፣ ይህ ወንዝ («ጤና ወንዝ» ተብሎ) ከኖኅ ልጆች ከሴምና ከያፌት ርስቶች መካከል የሆነው ጠረፍ ይሠራል። ጠረፉም ከዚያ ከምሥራቁ ጫፍ ቀጥታ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። በኩፋሌ 9፡21 ደግሞ፣ ከምሥራቁ ነጥብ እስከ መነሻው ድረስ ከዚያም ቀጥታ ወደ ስሜን የሆነ መስመር ከያፌት ልጆች ከጋሜርና ከማጎግ ርስቶች መካከል የሆነው ጠረፍ ነበር። ይህ በተለይ በአራማይስጥ ትርጉም ይታያል።
Remove ads
ነጥቦች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads