ጎርጎራ

ጎርጎራ ደብረ ሲና ማርያም ቤ/ክ From Wikipedia, the free encyclopedia

ጎርጎራ
Remove ads

ጎርጎራ ወይም ጐርጎራ (የድሮው ጎርጎራ) በጣና ሐይቅ ሰሜን የሚገኝ ልሳነ ምድርና ከተማ ነው። ጎርጎራ ከማሪያም ግምብ (አዲሱ ጎርጎራ) 5ኪሎ ሜትር በስተ ሰሜን ምስራቅ ሲገኝ፣ ከደብረሲና ደግሞ 5ኪሎሜትር በስተ ምዕራብ ይገኛል።

Quick facts

ታሪክ

እድሜያቸው ከ140፣000 እስከ 230፣000 የሚገመቱ የድንጋይ መሳሪያወች በጎርጎርጎራ እንደተገኙ ይጠቀሳል። ከክርስቶስ ልደት በፊት 7000 ዓ.ዓ. ጀምሮ የሸክላ ስራ ውጤቶች በአካባቢው ይመረቱ እንደነበር ከአካባቢው በተገኙ ናሙናወች ተነስቶ የኖርዲክ አፍሪካ ኢንስቲቱት ይዘግባል [1]

ወደ ቅርቡ ዘመን ስንመጣ፣ ጎርጎራ በዐፄ በእደ ማርያም ዜና መዋዕል ላይ ተጥቅሶ የሚገኝ ሲሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለጥንቶቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ማረፊያ እየሆነ መጥቶ በመጨረሻ በአጼ ሱሰንዮስ የአገሪቱ ዋና ከተማ ለመሆን የበቃ ክፍል ነው [2]። የመንዳባ ገዳም በዚሁ ልሳነ ምድር ሲገኝ፣ በ1924 አካባቢውን ጎብኝቶ የነበረው የእንግሊዙ ቺዝማን የገዳሙ አለቃ ፍጹም ስልጣን የነበራቸውና ህግን አምልጦ ገዳሙ ውስጥ የተጠለለ ሰው ማንም እንደማይነካው እንደነበር ይዘግባል[3]። አጼ ሱሰንዮስዋና ከተማቸውን በ1604 ከጉዛራ ወደ ጎርጎራ እንዳዛወሩ በታሪክ ይጠቀሳል። በኋላም በልጃቸው በፋሲልደስ ዘመን መጀመሪያ በዋና ከተማነት የቀጠለ ቢሆንም ቅሉ አጼ ፋሲል ጎንደር ከተማን በዋና ከተማነት በመቆርቆራቸው ዋና ከተማነቱ አቆመ። ለከተማው መዛወር የወባ በሽታ በአካባቢው መኖር እንደምክንያትነት ይገመታል[4]


Remove ads

አዲሱ ጎርጎራ (ማርያም ግምብ)

Thumb
የማርያም ግምብ (ሱሰንዮስ ቤተመንግስት) አቅድ
Thumb
የማርያም ግምብ ቅሪት በአሁኑ ዘመን

አዲሱ ጎርጎራ ከድሮው ጎርጎራ 5ኪ.ሜ. በስተ ደቡብ ምዕራብ የሚገኝ ነው። በዚህ ቦታ የሱሰንዮስ ግምብ ወይንም ማርያም ግምብ በካቶሊኩ የፖርቱጋል ጳጳስ ፔድሮ ፔዝ በ1612ዓ.ም. ተገነባ። ከ2 ዓመት በኋላ አጼ ሱሰንዮስ ሃይማኖታቸውን ወደ ካቶሊክነት ቀየሩ። ጀስዩቱ ቴሌዝ እንደመዘገበ፣ የግንቡ መታነጽ በፖርቱጋሎቹ ዘንድ የታቀደው አጼ ሱሰንዮስ ከጦርነት ተመልሰው ግንቦት፣ 1606ዓ.ም. በአካባቢው ከሰራዊታቸው ጋር እንደሰፈሩ ነበር። ፔድሮ ፔዝ ለህንጻው ስራ ነጭ አለትና የሚያጣብቅ ሸክላ አፈር እንደተጠቀመ ይገልጻል። ቤተ መንግስቱ የምድርና የፎቅ ክፍሎች የነበሩት ሲሆን ጣሪያው ለጥ ያለ ነበር።

መጋቢት፣ 1612 ዓ.ም. ፔድሮ ፔዝና ሰራተኞቹ አንስተኛ የካቶሊክ ካቴድራል ከቤተመንግስቱ አጠገብ አሰሩ[5]። ቤተመንግስቱንና ቤተክርስቲያኑን የሚከፍል፣ መስኮት የሌለው ግምብ ነበር።


Remove ads

የውጭ ንባብ(እንግሊዝኛ)

ማጣቀሻ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads