ጦር መሳሪያ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ጦር መሳሪያ ለውጊያ የሚውል የመሳሪያ አይነት ሲሆን፣ በውስጡ ሚገባውን ጥይት በባሩድ ፈንጂ ኃይል ተጠቅሞ በከፍተኛ ፍጥነት በማስወንጨፍ ጉዳት ያደርሳል።

የመጀመሪያዎቹ የጦር መሳሪያዎች በ10ኛው ክፍለ ዘመን ቻይና ውስጥ የተሰሩ ሲሆን፣ ጥቁር ባሩድን እንደ ፈንጅ ይጠቀሙ ነበር። ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች በአብዛኛው ጭስ አልባ ባሩድን ይጠቀማሉ እንዲሁም አብዛኛዎቹ (ከምንጃር ጠመንጃ(ሾት ጋን) በስተቀር) ስርስር አፈሙዝ አላቸው። ይህ ስርስር ጥይቱ በሚወነጨፍበት ጊዜ እንዲሽከረከር በማድረግ አቅጣጫውን ጠብቆ እንዲጓዝና ሩቅ ዒላማ በትክክል እንዲመታ ያስችለዋል።
Remove ads
የጦር መሳሪያዎች ምደባ
የጦር መሳሪያዎች በተለያዩ መስፈርቶች ይመደባሉ። ዋና ዋናዎቹ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
በመጠን እና በአጠቃቀም
ይህ ምደባ የጦር መሳሪያዎቹን አንድ ወታደር በቀላሉ ሊሸከማቸው ይችላል ወይ የሚለው ላይ ይመሰረታል።
- ቀላል የጦር መሳሪያዎች፦ አንድ እግረኛ ወታደር ብቻውን በቀላሉ ሊሸከማቸውና ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ናቸው። እነዚህም "ትናንሽ የጦር መሳሪያዎች" በመባል ይታወቃሉ።
- ከባድ የጦር መሳሪያዎች፦ በመጠን በጣም ግዙፍና ከባድ በመሆናቸው አንድ ሰው ብቻውን ሊሸከማቸው አይችልም። በሚተኩሱበት ጊዜ የሚያስከትሉት እርግጫ ከፍተኛ ስለሆነ፣ ተንቀሳቃሽና ውጤታማ ለመሆን እንደ ተሽከርካሪ፣ ድጋፍ ወይም መደብ ይፈልጋሉ።
በማቀባበያ
ይህ ምደባ አንድ መሳሪያ ጥይቶችን እንዴት ወደ አፈሙዙ እንደሚያስገባና እንደሚተኩስ ላይ ያተኩራል።
- አንድባንድ የሚሰራ(በተለምዶው ቁመህ ጠብቀኝ)፦ ተጠቃሚው እያንዳንዱን ጥይት ከተኮሰ በኋላ ያገለገለውን ጥይት አስወጥቶ አዲስ ጥይት በእጅ ማስገባት አለበት።
- ከፊል-አውቶማቲክ፦ ቃታው ሲሳብ አንድ ጥይት ብቻ ይተኩሳል፣ ነገር ግን መሳሪያው በራሱ አዲስ ጥይት ያቀባብላል። ድጋሚ ለመተኮስ ቃታው ተለቆ ድጋሚ መሳብ አለበት።
- ሙሉ-አውቶማቲክ፦ ተጠቃሚው ቃታውን እስካለቀቀ ድረስ መሳሪያው ያለማቋረጥ እያቀባበለ እሩምታ መተኮሱን ይቀጥላል።
Remove ads
ዋና ዋና የጦር መሳሪያ ዓይነቶች

የእጅ ሽጉጦች
በአንድ እጅ ለመያዝና ለመተኮስ የተሰሩ አጫጭር የጦር መሳሪያዎች ናቸው።
- ፒስቶል፦ ጥይቶቹ በመጋዘን (ካዝና) ውስጥ ተደርድረው የሚቀመጡ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ጥይት ከተተኮሰ በኋላ ቀጣዩ በራሱ ጊዜ ወደ መተኮሻው ቦታ ይገባል።
- ሽክርክሪት ሽጉጥ (ሪቮልቨር)፦ ጥይቶቹ በሚሽከረከር ከበሮ መሰል ክፍል ውስጥ ይቀመጣሉ። ቃታው ሲሳብ ከበሮው እየዞረ አዲስ ጥይት ወደ መተኮሻው ቦታ ያመጣል።
ረጅም የጦር መሳሪያዎች

በስደፍ ተደግፈው የሚተኮሱ እና ረጅም አፈሙዝ ያላቸው መሳሪያዎች ናቸው።
- ጠመንጃ፦ አፈሙዙ ውስጡ ስርስር ነው፤ ይህም ጥይቱ እየተሽከረከረ እንዲወጣ በማድረግ ርቀት ላይ ያለን ዒላማ በትክክል ለመምታት ያስችላል።
- አልሞ ተኳሽ ጠመንጃ :- እነዚህ ጠመንጃዎች የተሰሩት ለረጅም ርቀት ተኩስ ከፍተኛ ትክክለኝነት እንዲኖራቸው ተደርገው ነው
- የምንጃር ጠመንጃ:- ከሌሎች የጦር መሳሪያዎች የሚለየው ዋነኛ ባህሪው የአፈሙዙ ውስጣዊ ክፍል ልስልስ ያለ መሆኑ ነው።ይህ መሳሪያ የሚተኩሰው "የምንጃር ጥይት" ሲሆን፣ ይህ ጥይት በውስጡ በርካታ ትናንሽ የብረት ፍንጣሪዎችን (በአማርኛ ሽሮ) በአንድ ላይ የያዘ ነው። እነዚህ "ሽሮዎች" ከአፈሙዙ ከወጡ በኋላ ስለሚበተኑ፣ በአጭር ርቀት ላይ ተንቀሳቃሽ ዒላማዎችን ለመምታት ከፍተኛ ውጤታማነት አላቸው። በእንግሊዝ አፍ ሾት ገን ይባላል።
- ቅላል-መትረየስ፦ አነስተኛ እና ቀላል ሆኖ ነገር ግን እንደ መትረየስ ፈጣን እሩምታ መተኮስ የሚችል መሳሪያ ነው። ከጠመንጃ የሚለየው የሚጠቀመው የሽጉጥ ጥይቶችን በመሆኑ ነው።
- መትረየስ፦ ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ እሩምታ መተኮስ የሚችል፣ ሙሉ-አውቶማቲክ መሳሪያ ነው። ብዙውን ጊዜ የመደብ ድጋፍ ይፈልጋል።
Remove ads
ዓለም አቀፍ አምራቾች እና ስርጭት
ታዋቂ አምራቾች
በዓለም ላይ ካሉ የጦር መሳሪያ አምራቾች መካከል ዋና ዋናዎቹ ብራውኒንግ፣ ሬሚንግተን፣ ኮልት፣ ሩገር፣ ስሚዝ ኤንድ ዌሰን (አሜሪካ)፤ ሄክለር እና ኮክ፣ ዋልተር (ጀርመን)፤ ግሎክ (ኦስትሪያ)፤ በሬታ (ጣሊያን)፤ ኖሪንኮ (ቻይና)፤ እንዲሁም ክላሽንኮቭ (ሩሲያ) ናቸው።
የጦር መሳሪያዎች ስርጭት
እ.ኤ.አ. በ2018 የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው፣ በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የጦር መሳሪያዎች ይገኛሉ።
- 857 ሚሊዮን (85%) የሚሆኑት በሰላማዊ ሰዎች እጅ ይገኛሉ። ከዚህ ውስጥ 393 ሚሊዮኑ የአሜሪካ ዜጎች እጅ ላይ ነው።
- 133 ሚሊዮን (13%) የሚሆኑት በጦር ኃይሎች ቁጥጥር ስር ናቸው።
- 23 ሚሊዮን (2%) የሚሆኑት በሕግ አስከባሪ ተቋማት እጅ ይገኛሉ።
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads