ጳውሎስ ኞኞ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ጳውሎስ ኞኞ
Remove ads

ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ ኅዳር 11 ቀን 1926 ዓ.ም ቁልቢ አካባቢ ተወለደው ድሬዳዋ ከተማ አደጉ። በጣም ቆንጆ ስለነበር የልጅነት ስሙ አማረ ይባል፡ ከጊዜ በኋላ ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ስሙ ጳውሎስ ሊባል ችሎአል።

ጣሊያን ወረራ ምክንያት ትምህርታቸውን ከ4ኛ ክፍል በላይ ለመቀጠል አልቻሉም ነበር። ብልህ አዕምሮና የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ሰው ስለነበሩ፤ በልጅነታችው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጣሊያንን ሲገድሉ ወይንም ሲማርኩ ሥዕል በመሣል ያሳዩ ነበር። ጳውሎስ ካላቸው የጽሑፍ ጥማት የተነሳ የ«ድምጽ ጋዜጣ» አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር። ጋዜጦች ላይ ከጽሑፍ አቅራቢነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። በተለይ «አንድ ጥያቄ አለኝ» በሚለው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አምዳቸው ላይ ብዙ ታዋቂነትን አግኝተዋል።  አቶ ጳውሎስ ኞኞ ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ዕድገት የነበራቸውን ተሰጥኦ በአግባቡ በሥራ ላይ ያዋሉ እውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ።[1] እኚህ ታዋቂ ሰው በተወለዱ በ58 ዓመታቸው ሞቱ።
Thumb
ጳውሎስ ኞኞ (በስተግራ)
Thumb
አቶ ጳውሎስ ኞኞ

አቶ ጳውሎስ የጌታችው ሚስቶች በሚል ርዕስ ያሳተሟትን መጽሐፍ፤ «ከታተመችበት ወር አንሥቶ ላንድ ዓመት የመጽሐፌ መብት የግሌ ነው፡ ከአንድ ዓመት በኋል መብቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይሁን፡ ከወሰንኩት ጊዜ በኋላ አሳትሞ ለመሸጥ የፈለገ ሁሉ ከድርሰቴ ሳይቀንስም ሆነ ሳይጨምር ሊያራባው ይችላል። ስሜን ሳይሰርዝ 'አሳታሚውን እገሌ' ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ ከፈለገ እንዲያራባት የደራሲነት መብቴን ልቅቄአለሁ፡ አሳታሚው የግሉን የመግቢያ ሐተታ በስሙ ቢጽፍ እኔም ሆንኩ ወራሼ አንቃወምም።» ብለዋል

Remove ads

የጳውሎስ ኞኞ ድርሰቶች

ከጋዜጠኝነታቸው ጎን ለጎን በድርሰትና በታሪክ ጸሐፊነታቸውም ፲፱ መጻሕፍት የታተመላቸው ሲሆን ሁለቱ ካረፉ በኋላ የታተሙ ናቸ። ለሕዝብ የሚሆኑ ዕውቀት ተኮር መጻሕፍት በማቅረብ ይታወቁ የነበሩት አቶ ጳውሎስ ኞኞ ካረፉ ከ፳ ዓመታት በኋላ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸውንና ወደውጭ አገር የላኳቸውን ደብዳቤዎች የሚያሳዩት ሁለት መጻሕፍት በአስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ታትመዋል።[2]

አጫጭር ልብ ወለዶች

  • ከሴቶቹ አምባ
  • የአራዳው ታደሰ
  • የጌታቸው ሚስቶች
  • ድብልቅልቅ
  • የኔዎቹ ገረዶች

ታሪካዊ መጻሕፍት

ጥቅስ

ስለጸሐፊነት ባህሪያቸው ሲጽፉ፦ «'ይምሰል አይምሰል የጠይብ እጅ ከከሰል' እንደሚባለው እጄ እንደልማድ ሆኖበት መሞጫጨርን ይወዳል፡ ያን ሟጫራዬን ደግሜ ካነበብኩ ቀድጄ መጣል ነው፤ ይሰለቸኛል፡ እጠለዋለሁ፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ በማርቀቅ የጻፍኳትን እንድትታተም እፈርድባታለሁ። ምናልባት አባጣ ጎባጣ ሆኖ አላስኬድ የሚል ገደላገደል ቢያጋጥማችሁ በደምዳሜ እመር እያላችሁ አላፉት።» [3]

ማስታወሻ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads