ፈርዖን

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ፈርዖን ማለት የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ነው። ይህ ከግብጽኛ «ፐር-ዓ» ከ«ፐር» (ቤት) እና «ዓ» (ታላቅ) ወይም «ታላቁ ቤት» ደረሰ። ፐር-ዓ መጀመርያ ቤተ መንግሥት ለማመልከት ሲሆን፣ ከ1400 ዓክልበ. በኋላ ንጉሡን ፐር-ዓ ይሉት ጀመር። ስለዚህ ከዚያ በፊትም የነገሡት ግብጻዊ ንገሥታት ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረትአብርሐም፣ በዮሴፍ ወይም በሙሴ ዘመን የነበሩት ነገሥታት ደግሞ «ፈርዖን» ተብለዋል። አሁንም ማናቸውም ግብጻዊ ንጉሥ ከመጀመያው ንጉሣቸው ከናርመር ወይም ሜኒስ ጀምሮ የዛኔው ማእረግ ባይሆንም ዛሬ ግን «ፈርዖን» እንላቸዋለን።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads