ፋሲል ግምብ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ፋሲል ግምብ
Remove ads

ፋሲል ግምብ ፋሲል ግቢ ውስጥ ካሉት ግምቦች ትልቁና ቀደምቱ ነው። አጼ ፋሲለደስ የአገሪቱ መዲናን ከቦታ ቦታ መዛወር በመሰልቸት በመጨረሻ ጎንደር ከተማ ላይ የረጋ ማዕከል በ1628ዓ.ም. አቋቋሙ። በ1640ወቹ መጀመሪያ ፋሲል ግምብን በከተማው ማዕከል አሰርተው አስጨረሱ። ፋሲል፣ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ግምቦችንና ከ7 የማያንሱ ቤተክርስቲያኖችን እንዲሁም 7 ድልድዮችንና የአክሱም ጽዮንን ግንብ አሰርተዋል።

Thumb
ፋሲል ግምብ በ1894ዓ.ም.

Thumb

*ግምጃ ቤት ማርያም
*ፋሲል ቤተክርስቲያን
*ድልድይ
*ቋል (ጋብቻ)ቤት
*እልፍኝ ጊዮርጊስ
አዋጅ መንገሪያ*
ክረምት ቤት*
*አዋጅ ነጋሪ
*ጃን ተከል ዋርካ
*ሰሜን
አደባባይ ተክለ ሃይማኖት

ፋሲል ግምብ ፋሲል ግቢ ውስጥ በስተ ደቡብ የተቀመጠ ሲሆን ሁለት ፎቅና 123 ደረጃዎች አሉት። ከጣሪያው ላይ ባለው መመልከቻ በረንዳ እስከ ጣና ሐይቅ ድረስ መመልከት ይቻላል። በውስጡ 20 ክፍሎች ሲኖሩት ከላይ የሚገኙት ክብ ክፍሎች ለጸሎትና መሰል የሃይማኖት ስራዎች ይጠቅም ነበር። ከላይ ያለው ጠፍጣፋው ክፍል ንጉሱ ለህዝቡ የሚናገሩበት ነበር፡

Thumb
ፋሲል ግምብ በአሁኑ ዘመን
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads