ፒሬኔ ተራሮች

From Wikipedia, the free encyclopedia

ፒሬኔ ተራሮች
Remove ads

ፒሬኔ ተራሮችፈረንሳይና በእስፓንያ መካከል የሚገኝ የተራሮች ሰሰለት ነው። አንዶራ የሚባለው ትንሽ አገር ደግሞ በፒሬኔስ ይገኛል።

Thumb
የፒረኔስ ካርታ

ስያሜ

ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ (60 ዓክልበ. ግድም) እንደ ጻፈው (V. 35) በጥንት ከእረኞች አለመጠንቀቅ የተነሣ አንድ ታላቅ እሳት ዙሪያውን በሙሉ ስላቃጠለ የተራሮቹ ስም ከ«እሳት» (ፒር ወይም ፑር በግሪክኛ) መጣ። በመቃጠላቸው ምክንያት የብር ፈሳሾች ተገለጡ። የፊንቄ ሰዎች ሲደርሱ ብር እንደ ርካሽ ዕቃ አገኝተውት ከኗሪዎቹ በንግድ ገዝተውት እንደ በለጠጉ ይለናል።

በኋላ ግን የሮሜ ደራስያን ሉካን (60 ዓ.ም.) እና ሲልዩስ ኢታሊኩስ (90 ዓ.ም.) ሌላ ትውፊት ጻፉ። ሄርኩሌስ ሊቢኩስጌርዮንን ከብት ለመውሰድ እየሄደ የተራሮች አውራጃ ንጉሥ ቤብሩክስ ጋበዘው። ሄኩሌስ ግን ሰክሮ የንጉሡን ሴት ልጅ ፒሬኔ በግድ ጠልፎ ከኅፍረቷ በተራሮቹ እስከ መሞቷ ድረስ ተንቀዋለለች። ስምዋን ለተራሮቹ ሰጠች ብለው ጻፉ።

ዘመናዊ የአውሮፓ ሊቃውንት ግን በኬልቶች ቋንቄ «ቢሬን» ማለት «ኮረብታ፣ ተራራ» እንደ ነበር ይላሉ።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads