From Wikipedia, the free encyclopedia
የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ (ማ.ስ.ኤ.) በኢትዮጵያ መንግሥት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ስር የሚገኝ ኤጀንሲ ወይም ባለስልጣን ሲሆን ተልዕኮው ለኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዕድገት አሰሳ የሚያገለግሉ የሕዝብ ቆጠራ፣ የዋጋ መረጃ ማሰባሰብ፣ የቤተሰብ ፍጆታና ወጪን ማጥናትና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ማከናወን ነው። በተጨማሪም ኤጀንሲው በዘርፉ ባለሙያዎችን የማሰልጠን ኃላፊነት አለበት። በአሁኑ ጊዜ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሳሚያ ዘካሪያ ናቸው።
ከየካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. በፊት ኤጀንሲው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ በመባል ይታወቅ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ኤጀንሲው በሚከተሉት ፳፭ ቦታዎች ቅርንጫፎች አሉት፦ አዲስ አበባ፣ አምቦ፣ አርባ ምንጭ፣ አሰበ ተፈሪ፣ አሳይታ፣ አሶሳ፣ አዋሳ፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣ ድሬ ዳዋ፣ ጋምቤላ፣ እንደ ሥላሴ፣ ጋምቤላ፣ ጎባ፣ ጎንደር፣ ሐረር፣ ሆሳዕና፣ ጅጅጋ፣ ጅማ፣ መቀሌ፣ ሚዛን ተፈሪ፣ ናዝሬት፣ ነገሌ፣ ነቀምት እና ሶዶ።[1]
አገር አቀፍ የሕዝብና መኖሪያ ቆጠራ እ.ኤ.አ. በ1984፣ 1994፣ 2007 የተከናወነ ሲሆን የመጨረሻዎቹ ሁለት ቆጠራዎች ዝርዝር መረጃ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.