From Wikipedia, the free encyclopedia
የራዲዮ ሞገዶች ልክ እንደ ብርሃን እና ኤክስሬይ የኤሌክትሮመግነጢስ ማዕበል አካል ናቸው። ልዩነታቸው ሞገዳቸው በጣም ረጅም መሆኑ ነው።
በዓይን የሚታየው ብርሃን የሞገድ ርዝመት ከሰው ልጅ ፀጉር እጅግ የሚያንስ፣ ከማይክሮ ሜትር በታች የሆነ ጥቃቅን ነው። የራዲዮ ሞገድ በአንጻሩ ሞገዱ በሴንቲሜትርና በሜትር የሚለካ ሲሆን በአይን ግን አይታይም።
የራዲዮ ሞገድ ተቀባይ አንቴናወች ሲተለሙ ለሚቀበሉት ሞገድ ርዝመት ተመሳሳይ ቁመት እንዲኖራቸው ተደርጎ ነው። ለዚህ ነው የራዲዮ አንቴናወች ረጅም የሆኑት። ርዝመታቸው ከሚቀበሉት ሞገድ አንጻር አጭር የሆኑ አንቴናወች ሞገድ የመቀባልቸው ሃይል የተዳከመ ነው።
ሰው ሰራሽ የራዲዮ ሞገዶች መረጃን ለመለዋወጥና ዜና ለማሰራጨት ሲያገለግሉ ከ100 አመት በላይ አስቆጥረዋል። ራዲዮን፣ ቴሌቪዥን፣ ሳተላይቶች፣ የዕጅ ስልኮች ወዘተ መረጃን የሚያሰራጩትና የሚቀበሉት እኒህን ሞገዶች በመጠቀም ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የራዲዮ ሞገዶች ነገሮችን "ለማየት"ም ሲያገለግሉ ይታያሉ። ራዳር ከኒህ ወገን ሲሆን የሚሰራውም የራዲዮ ሞገዶችን ርቀው ወዳሉ ነገሮች በመላክ ነጥረው ሲመለሱ የሚወስዱትን ሰዓት በመለካት ሩቅ ያሉ ነገሮችን "ለማየት" ይረዳል። በተረፈ ራዳር መሬት ውስጥ ተቀብሮ ያለን ቤንዚን መርምሮ ለማግኘት፣ የአፈርን ኬሚካላዊ ባህርይ ለማወቅ ይረዳል።
ራዲዮ ሞገዶች ሰው ሰራሽ ብቻ ሳይሆኑ፣ በተፈጥሮም ይገኛሉ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.