ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ የካሪቢያን ባህር ደሴት አገር ሲሆን ዋና ከተማው ኪንግስታውን ነው። ሰይንት ቪንሰንት ዋናው ትልቁ ደሴት ነው።
Quick Facts ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝSaint Vincent and the Grenadines ...
ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: "Saint Vincent, Land so beautiful" | ||||||
ዋና ከተማ | ኪንግስታውን | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ | |||||
መንግሥት {{{ ንግሥት አገረ ገዥ ጠቅላይ ሚኒስትር |
ንግሥት ኤልሣቤጥ ፍሬድሪክ ባለንታይን ራልፍ ጎንሳልቨስ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
389 (184ኛ) |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2012 እ.ኤ.አ. ግምት |
109,991 (181ኛ) |
|||||
ገንዘብ | የምሥራቅ ካሪቢያን ዶላር | {{{የምንዛሬ_ኮድ}}} | ||||
የሰዓት ክልል | UTC −4 | |||||
የስልክ መግቢያ | +1 784 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .vc |
Close
የብሪቲሽ ኮመንዌልዝ አባል ሲሆን ከንግሥት ኤልሣቤጥ ግዛቶች አንዱ ነው። የሀገሩ ዋና ምርት ሙዝ ነው፣ እንዲሁም የቱሪዝም መድረሻ ነው። የአገር ሥራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ቢሆንም የሕዝብ መነጋገሪያ የቪንሰንት ክሬዮል ነው።
በአገሩ ታሪክ፣ እስከ 1711 ዓም ድረስ የደሴቶች ኗሪዎች የካሪቦች ብሔር አውሮጳውያን እንዳይሠፍሩባቸው ከለከሉ። በቋንቋቸው ሰይንት ቪንሰንትን «ዮውሎውማይን» ይሉት ነበር። በመርከብ አደጋ ምክንያት ግን ከባርነት ያመለጡ አፍሪካውያን በደሴቶቹ ደርሰው ከካሪቦቹ ጋር ተቀላቀሉ። እነርሱም የጋሪፉና ብሔር ተብለው በኋላ (1789 ዓም) ወደ ሆንዱራስና ቤሊዝ አካባቢ በመካከለኛ አሜሪካ ጠፈፍ ተሰደዱ። የፈረንሳይ ሰዎች በ1711 ዓም ሠፈሩበት፣ ዩናይትድ ኪንግደም በጦርነት በ1746 ዓም ያዘው፣ እንደገና ከ1771 እስከ 1775 ዓም ድረስ ወደ ፈረንሳይ ተመለሰ፤ ከዚያም ጀምሮ የዩናይትድ ኪንግደም ቅኝ ግዛት ሆኖ እስከ 1971 ዓም ድረስ ቆይቶ ነበር።
- (ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ!)